top of page

የካቲት 28፣2016 - ቢጂአይ ኢትዮጵያ የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ  እና ፉብሪካ የሽያጭ ሂደት የተቋረጠው ገዢው "የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነው "አለ

  • sheger1021fm
  • Mar 7, 2024
  • 2 min read

 

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ሜክሲኮ የሚገኘው የዋና መስሪያ ቤት ህንፃ  እና ፉብሪካ ለፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ  ለመሸጥ ጀምሮት የነበረው  የሽያጭ ሂደት የተቋረጠው ገዢው "የሽያጭ ውሉን ለመፈረም ፍቃደኛ ባለመሆኑ ነው "አለ።

 

ሰኔ 2015 ዓ.ም በተፈረመ የቀብድ ውል ስምምነት  ከ 8 ወራት በላይ ፈጅቷል ሲል ቢጂአይ ኢትዮጵያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስረድቷል።

 

ቢጂአይ የድርድር ሂደቱን እንዲጠናቀቅ እና በተዋዋይ ወገኖች መካከል የቀረበውን የሽያጭ ውል እንዲፈረም ለፐርፐዝ ብላክ በተደጋጋሚ በይፋ ጥያቄ አቅርቤያለሁ ብሏል።

 

የሽያጭ ውሉ በቢጂአይ በኩል የሚጠበቀውን የታከስ ከሊራንስ ከሚመለከተው የመንግስት አካል ለማግኘት እንዲቀርቡ ከሚጠየቁ ሰነዶች ውስጥ እንዱ  መሆኑንም ኩባንያው እስታወሷል።

 

በገዢ እና ሽያጭ መካከል ሊፈረም የሚገባው የሽያጭ ውል ቢጂአይ የካፒታል ገቢ ግብር ታክስ ከገቢዎች ሚኒስቴር እንዲያገኝ አስፈላጊ ቅድመ ሁኔታ መሆኑንም ጠቅሷል።

 

በሰነዶች ምዝገባና ማረጋገጫ የሚመዘገበው የሽያጭ ውል የታክስ ከሊራንስ ከተገኘ በኋላ የሚፈፀም ነው ሲልም ኩባንያው አስረድቷል።

 

በፐርTዝ ብላክ  ህንፃውን ለመግዛት በቂ ፋይናንስ እንደሚያቀርብ አሳውቆን ነበር ያለው ቢጂአይ ይሁን እንጂ ድርጅቱ ለግብይቱ አስፈላጊውን ከፍያ ለመፈፀም የሚያስችል አቅም እንዳለው የሚያሳይ ምንም አይነት ማስረጃ አላቀረበልኝም ብሏል።



የሽያጭ ሂደቱ ሙሉ ለሙሉ መቋረጡን፣ይህም ሂደት እልባት ሲያገኝ ፈብሪካው ለሌላ ገዢ ለገበያ እንደሚቀርብ የኩባንያ ሀላፊዎች ለጋዜጠኞች አስረድተዋል።

 

ፐርፐዝ ብላክ ሚክሲኮ ለሚገኘው የቢጂአይ ዋና መስሪያ ቤት ግዢ ቅድመ ክፍያ የፈፀመው የአጠቃላይ ዋጋውን 20 በመቶ ወይንም 1 ቢሊዮን ብር ውሉ በመቋረጡ በስመምነቱ  ውል መሰረት እጣ ፈንታው ይወሰናል ተብሏል።

 

ፐርፐዝ ብላክ በአዲስ አበባ ሜክሲኮ የሚገኘውን የቢጂአይ ኢትዮጵያን ዋና መሥሪያ ቤት በጨረታ አሸንፎ አንደገዛው አና  ለዚህም 1 ቢሊዮን ብር ቅድመ ክፍያ መፈጸሙን መናገሩ ይታወሳል፡፡

 

በቦታው ላዮም  ባለ 115 ወለል የከገበሬው ታወር እንዲሁም ለመኖሪያ፣ ለንግድ፣ ለመዝናኛ እንዲሁም፤ ለልዩ ልዩ አገልግሎቶች የሚውሉ 6 ሕንጻዎችን ለመገንባት ማሰቡን ተናግሮ ነበር፡፡

 

የቢጂአይን ኢትዮጵያ ሜክሲኮ የሚገኘውን የማምረቻ እና ዋና መስሪያ ቤቱን ለፐርፐዝ ብላክ የሸጠው  በውሃ አቅርቦት ውስንነትና በሎጂስቲከስ ችግሮች ምክንያት ነው ብለው  ዋና ስራ አስፈፃሚው ሄርቬ ሚልሃድ  መናገራቸው ይታወሳል።

 

 

ንጋቱ ሙሉ

 

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page