top of page

የካቲት 27 2017 -የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ግብር ያልከፈሉትን ደንበኞቹን ከሀገር እንዳይወጡ አገደ።

  • sheger1021fm
  • Mar 6
  • 1 min read

የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ግብር ያልከፈሉትን ደንበኞቹን ከሀገር እንዳይወጡ አገደ።


ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ የታክስ ዕዳ ያለባቸው 62 ግብር ከፋዮች ከሀገር እንዳይወጡ የእግድ ትዕዛዝ ማስተላለፉም ተሰምቷል።


ቢሮው የሚገባኝን ከ3.2 ቢሊዮን ብር በላይ የግብር ዕዳ ያለባቸውን ደንበኞች በተደጋጋሚ ጥሪ ባደርግም ዕዳቸውን ለመክፈል ፈቃደኛ አልሆኑም ብሏል።


እነዚህ 62 ግለሰቦች በታክስ አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 983/2008 አንቀፅ 44 ንዑስ አንቀፅ ከ1-3 ለተቋሙ በተሰጠ ስልጣን መሰረት ከሀገር እንዳይወጡ ለፌዴራል የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዝርዝራቸውን አስተላልፏል ተብሏል።

ቢሮው በ2017 በጀት ዓመት የግብር ዕዳቸውን የሚሰወሩ ግብር ከፋዮችን በአግባቡ በመከታተል ግዴታቸውን እንዲወጡ የዕዳ ክትትልና አስተዳደር የስራ ክፍልን በአዲስ መልክ አደራጅቻለሁ ብሏል፡፡


ባለፉት ስድስት ወራት ከ6.4 ቢሊዮን ብር በላይ ዕዳ መሰብሰቡን ተናግሯል።


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Σχόλια


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page