top of page

የካቲት 27፣2017 - ኢትዮ ቴሌኮም እድሜው 130 ዓመት መሙላቱን ምክንያት በማድረግ ዛሬ ሽልማቶች ለደንበኞቹ መስጠቱ ተሰማ።

ኢትዮ ቴሌኮም እድሜው 130 ዓመት መሙላቱን ምክንያት በማድረግ ከ 49.45 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ሽልማቶች ለደንበኞቹ መስጠቱ ተሰማ።


ኩባንያው 130ኛ ዓመት ክብረ-በዓሉን ምክንያት በማድረግ ከመስከረም 12 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ፕሮግራሙን አስጀምሮ ነበር።


ለደንበኞችም የኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ እና ኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃግብር ተዘጋጅቶ ነበር።

ሁለት ዘመናዊ ኤሌክትሪክ መኪኖችን እና አምስት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪዎችን ለዕድለኞች በሽልማት ሰጥቷል ተብሏል።


ኩባንያው  ዛሬ በኢትዮ 130 ሜጋ ፕሮሞ መርሃ ግብር ለእጣው ብቁ ለሆኑ 393,375 ልዩ ደንበኞች አንድ ቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እንዲሁም ለእጣው ብቁ ለሆኑ 540,566 ደንበኞች ሶስት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ ዕጣ ለእድለኞች አውጥቷል፡፡


በኢትዮ 131 ላኪ ስሎት ሽልማት መርሃግብር ደግሞ ለእጣው ብቁ ለሆኑ 226,970 ደንበኞች አንድ ቢ.ዋይ.ዲ ዘመናዊ የኤሌክትሪክ መኪና እንዲሁም ለእጣው ብቁ ለሆኑ 407,200 ደንበኞች ሁለት ባለ 3 እግር ተሽከርካሪ ዕጣ ለእድለኞች አውጥቷል ተብሏል።


ኩባንያችው ባለፉት አምስት ወራት 141 ዘመናዊ ስማርት ስልኮችን፣ በየቀኑ እና በየሳምንቱ በድምሩ 10.56 ሚሊዮን ብር የቴሌብር ኤሌክትሮኒክስ ገንዘብ እንዲሁም 1.18 ሚሊዮን የሞባይል ጥቅሎችን ሰጥቷል።


መርሃ ግብሩ አሁንም ይቀጥላል የተባለ ሲሆን ደንበኞች በኢትዮ 130 ፕሮሞ እና በኢትዮ 131 ላኪ ስሎት እየተጫወቱ ዘመናዊ የኤክትሪክ መኪናን ጨምሮ ልዩ ልዩ ሽልማቶችን ማሸነፍ ትችላላችሁ ተብላችኋል።



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page