የኢትዮዽያ አየር መንገድ ከቦይንግ ኩባንያ ጋር ይህን የአውሮፕላን ግዢ የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርሟል።
አውሮፕላኖቹ ነዳጅ ቆጣቢና እጅግ ዘመናዊ ቦይንግ 777-9 የተባሉ አውሮፕላኖች መሆናቸውን የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰው ተናግረዋል።
ኢትዮዽያ ከዚህ ቀደም አልነበራትም የተባሉት ግዙፍ ቦይንግ 777-9 በቁጥር 20 መሆናቸውን በስነስርዓቱ ላይ ሲነገር ሰምተናል።
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህን አይነቱን አውሮፕላን በመግዛት በአፍሪካ ቀዳሚው አየር መንገድ እንደሚያደርገው ተነግሯል።
ዋና ስራ አስፈፃሚ መስፍን ጣሰው የኢትዮዽያ አየር መንገድ ከቦይንግ ጋር ያለውን የረጅም ግዜ ወዳጅነትና አብሮ የመስራት ልማድ ተናግረው አየር መንገዱ ከዚህ ቀደም ባልነበረውና ወደፊት በሚገባው ግዙፍ ቦይንግ 777-9 አውሮፕላን በአፍሪካና በተቀረው አለም ሰማይ ለመብረርና የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ እንደሚረዳው አስረድተዋል።

በስምምነቱ የቦይንግ ምክትል ፕሬዝዳንት ብራድ ማክሙለን ኢትዮጵያ ከኩባንያው ጋር ያላትን ጥብቅ የስራ አጋርነት አንስተው አሁንም የኢትዮዽያ አየር መንገድ በቦይንግ ኩባንያ ላይ ያለውን መተማመን ዋጋ መስጠታቸውን ሲናገሩ ሰምተናል።
የ20ዎቹ አውሮፕላኖች ግዢ ወደ 11 ቢሊየን ደላር የሚጠጋ ነው ተብሏል።
ተህቦ ንጉሴ
Comments