top of page

የካቲት 28፣2016 - በዓለም አቀፍ ደረጃ በገዳይነቱ 4ኛ ደረጃን የሚይዘው የማህፀን በር ካንሰር በየዓመቱ 342 ሺህ ሴቶችን ይገድላል ተባለ

በዓለም አቀፍ ደረጃ በገዳይነቱ 4ኛ ደረጃን የሚይዘው የማህፀን በር ካንሰር በየዓመቱ 342 ሺህ ሴቶችን ይገድላል ተባለ፡፡


በየዓመቱ በበሽታው የሚጠቁ ሴቶች ቁትርም 604 ሺህ ነው ተብሏል፡፡


ይህንን ያለው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጤና ቢሮ ነው፡፡


90 በመቶ የሚሆኑት የበሽታው ተጠቂዎች በመካከለኛ እና በዝቅተኛ የኑሮ ደረጃ ላይ ያሉ ናቸው ያሉት የቢሮው ሃላፊ ዶክተር ዮሀንስ ጫላ በተለይም ችግሩ ከሰሀራ በስተደቡብ ባሉ የአፍካ ሀገራት በስፋት ይስተዋላል ብለዋል፡፡


በዚህም በአለም ላይ በአማካይ በየሁለት ደቂቃው አንዲት ሴት በማህፀን በር ካንሰር ህይወቷን እንደምታጣ ተነግሯል፡፡


በኢትዮጵያም ከጡት ካንሰር ቀጥሎ በገዳይነቱ ሁለተኛ ደረጃን የያዘ እንደሆነ እና በአመት 5,000 ሴቶች እንደሚሞቱ ሲነገር ሰምተናል፡፡


ፋሲካ ሙሉወርቅ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


bottom of page