top of page

የካቲት 26 2017 - ግጭትን መዘገብ ብቻ ሳይሆን ግጭትን ማስቀረት በሚያስችል ሁኔታ በመዘገብ የንግድ መገናኛ ብዙሃን ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Mar 5
  • 1 min read

ግጭትን መዘገብ ብቻ ሳይሆን ግጭትን ማስቀረት በሚያስችል ሁኔታ በመዘገብ የንግድ መገናኛ ብዙሃን ድርሻቸውን ሊወጡ ይገባል ተባለ፡፡


ይህ የተባለው ዛሬ የሰላም ሚኒስቴር እና የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን በቢሾፍቱ ከተማ ከጋዜጠኞችና ከመገናኛ ብዙሃን የስራ ሀላፊዎች ጋር እያደረጉት ባሉት ውይይት ላይ ነው፡፡


የመገናኛ ብዙሃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሳምሶን መኮንን(ዶ/ር) የንግድ መገናኛ ብዙሃን ግጭትን መዘገብ ብቻ ሳይሆን ግጭትን አስቀድሞ መከላከል ላይ ድርሻቸው ከፍተኛ ስለሆነ ሀላፊነታቸውን መወጣት አለባቸው ብለዋል፡፡


ሌላው በመድረኩ ላይ ንግግር ያደጉት የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ድኤታ ከይረዲን ተዘራ በበኩላቸው የንግድ መገናኛ ብዙሃን አሰባሳቢ እና አንድ የሚያደርጉ ትርክቶች ላይ መስራት አለባቸው ብለዋል፡፡

ኢትዮጵያና ኢትዮጵያዊነትን በመስበክ ከሚያለያዩ ይልቅ የሚያሰባስቡ ትርክቶች ላይ መስራት ከንግድ መገናኛ ብዙሃን ይጠበቃል ሲሉ ሚኒስትር ድኤታው አስረድተዋል፡፡


በመድረኩ ላይ የመገናኛ ብዙሃን ለሰላም ግንባታ ያላቸው ድርሻ በሚል ፅሁፍ ያቀረቡት በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የጋዜጠኝነት እና የኮሚዩኒኬሽን መምህር የሆኑት አንተነህ ፀጋዬ (ዶ/ር) የሀገር ጥቅም የሰላም ግንባታ እና የሀገር ደህንነት ላይ መስራት የመንግስት ወይንም የፖለቲካ አጀንዳ ሳይሆን መገናኛ ብዙሃን አጀንዳም ጭምር ነው ብለዋል፡፡


ለዚህም በአገር ግንባታ፣ በሰላም እና በአገራዊ ጥቅም ላይ መስራት ከመገናኛ ብዙሃን ይጠበቃል ሲሉ አስረድተዋል፡፡


ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page