top of page

የካቲት 26 2017 - ''ከመንግስት ይልቅ አላሰራ ያሉኝ የዘውግ ፖለቲካ አራማጆች ናቸው '' ኢዜማ

ገዢው ፓርቲ በሀገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ የታችኛው መዋቅር ላይ ጣልቃ እየገባ ነው ሲል ኢዜማ ከሰሰ፡፡


ፓርቲው ብሔራዊ የሥራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ስብሰባውን ማጠናቀቁን ተከትሎ ትናንት የካቲት 25 ቀን 2017ዓ.ም ባወጣው መግለጫው ገዢው የብልፅግና ፓርቲ ከዚህ ድርጊቱ እንዲቆጠብ አሳስቧል፡፡


የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( #ኢዜማ ) ለ3 ቀናት ባካሄደው የስራ አስፈፃሚ ኮሚት ስብሰባ በፓርቲው አሠራር ሒደት፣ በወቅታዊ ሀገራዊ የፖለቲካ ጉዳዮች ላይ እንዲሁም በቀጣይ ስለሚኖሩ ድርጅታዊ ተግባራት ላይ ተወያይቶ ውሳኔዎችም ማሳለፉን የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ አባል አብረሃም በርታ(ዶ/ር) ነግረውናል፡፡


በውይይቱ ከተነሱ ሃሳቦች መካከል እተካሄደ የሚገኘው ሃገራዊ ምክክር አንዱ ነው ያሉን ሃላፊው እንደ ሀገር አላግባቡ ያሉ ችግሮቻችን የሚፈቱት በንግግር ነው ብለን ስለምናምን ነው ኮሚሽኑን የምንደግፈው ብለዋል፡፡


ነገር ግን ገዢው ፓርቲ በተለይ በታችኛው መዋቅር ባሉ የምክክር ሂደቶች የራሱን ሰዎች በማስገባት፤ የራሱን የሆኑ #አጀንዳዎች እንዲቀርቡ እያደረገ በመሆኑ የኮሚሽኑ ተአማኒነት ላይ ተፅዕኖ ሊፈጥር ስለሚችል ከዚህ ድርጊቱ ሊቆጠብ ይገባል፤ ይህ ችግር በአዲስ አበባ፣ በኦሮሚያና በደቡብ በነበረው አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት ታይቷል ይላሉ ዶ/ር አብርሃም፡፡

ገለልተኝቱን አስጠብቆ ለመዝለቅ ይህንን ችግር እንዲፈታ ለሃገራዊ ምክክር ኮሚሽኑ ማሳወቁን የኢዜማ ስራ አስፈፃሚ አባሉ ዶ/ር አብርሃም ነግረውናል፡፡


ወደ ስልጣን መውጫ ብቸኛው መንገድ ምርጫ እንደሆነ የሚናገረው ፓርቲው አሁን ላሉ ችግሮች መፍትሄ ነው ብሎ የሚያምነውን ዜግነት ላይ መሰረት ያደረገ የፓርቲ አደረጃጀት ይዞ ለቀጣዩ ምርጫ ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመቅረብ የምርጫ አስተባባሪ ኮሚቴ በመሰየም ዝግጅት እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡


ከመንግስት ይልቅ አላሰራ ያሉኝ #የዘውግ_ፖለቲካ አራማጆች ናቸው የሚለው ፓርቲው፤ በየደረጃው በሚሰራቸው የፖለቲካ ስራዎች እንቅፋት እንደሆኑበት ተናግሯል፡፡


አልፎ አልፎም በተለይ በደቡብ አካባቢ ዘይሴ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በመንግስት አመራሮች አባሎቻችን ታስረውብናል፤ ይሁንና በየትኛውም አካባቢ የፅህፈት ቤት መዘጋት አላጋጠመንም ብለውናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. https://tinyurl.com/3vzfezyd


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Komentarze


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page