የካቲት 26 2017 - በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልልከባንኮች አንድ ሰው በቀን ከ500 ብር በላይ ማውጣት አይችሉም ተባለ
- sheger1021fm
- Mar 5
- 1 min read
Updated: Mar 14
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የኮንትሮባንድ ንግድ በመስፋፋቱና የጥሬ ገንዘብ እጥረት በማጋጠሙ እጃቸው ላይ ገንዘብ ያላቸው አትርፈው መሸጥ ጀምረዋል ተባለ፡፡
እንደማሳያም 90,000 ብር በ100,000 ብር ይሸጣል፡፡
ከባንኮች አንድ ሰው በቀን ከ500 ብር በላይ ማውጣት አይችሉም ተባለ፡፡
የህዝብ እንደራሴዎች ም/ቤት አባል እና የቦሮ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ የፖለቲካ ዘርፍ ሀላፊ መብራቱ አለሙ የጥሬ ገንዘብ እጥረት በባንኮች መፈጠሩን እና የኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋትን የተመለከቱት በምርጫ አካባቢያቸው በመተከል ዞን በመገኘት ባደረጉት ህዝባዊ ውይይት መሆኑን ለሸገር ነግረዋል፡፡
የኑሮ ውድነቱ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ተባብሷል የሚሉት የህዝብ እንደራሴው ይህንንም በህዝባዊ ውይይታችን ተመልክተናል ብለዋል፡፡
ሙሉ ዘገባወን ያድምጡ….
የኔነህ ሲሳይ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments