በኢትዮጵያ ከልብ ህክምና ጋር የተያያዙ ስራዎች ላይ የተሟላ አገልግሎት ለመስጠት በመንግስት የሚቋቋሙ ተጨማሪ ማዕከላት ያስፈልጋሉ ተባለ፡፡
በአገሪቱ ብቸኛ የሆነውና በጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የሚገኘው የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ከመንግስት የተወሰኑ ድጋፎች ባገኝም አገልግሎቱን እየሰጠሁ ያለሁት ከዜጎች በሚገኝ ድጋፍና በዓለም አቀፍ ለጋሾች እርዳታ ነው ብሏል፡፡
ማዕከሉ ቋሚ የሆነ በጀት ያልተመደበለትና በሚገኝ ድጋፍ ብቻ #የልብ_ህክምና አገልግሎቱን እየሰጠ እንደሚገኝም ተናግሯል፡፡
ከልብ ህመም ጋር የተያያዙ አብዛኛዎቹ ህመሞች ህክምና በሃገር ቤት ባለሙያዎች እንደሚሰጥ የኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል ሜዲካል ዳይሬክተር እና የህፃናት ስፔሻሊስት ሀኪም የሆኑት ዶክተር ሄሌዘር ሀይሌ ነግረውናል፡፡

አብዛኛዎቹ የህክምና መሳሪያዎች ከውጭ መምጣታቸው፣ ግብዓቱን የሚያመጣው አካል የመረጃ ስርጭቱ ላይ የተወሰነ ችግር አለው የህክምና ዓይነቶቹ እዚህ አገር እንደማይሰራ ተደርጎ የሚቀርብበት ሂደት አለ እሱ መቅረት አለበት ብለዋል፡፡
በኢትዮጵያ ውስጥ የማይሰሩ ውስን የሆኑ የልብ ንቅለ ተከላ ዓይነት ችግሮች ካልሆነ በስተቀር በአብዛኛው በኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች መሰራት የሚችሉ ናቸውም ብለዋል፡፡
ነገር ግን ያለው የሰው ኃይል በአገሪቱ የልብ ህክምና ለማግኘት ከሚጠባበቁ ሰዎች አኳያ ጥቂት ነው የሚሉት ዶክተር ሄሌዘር አሁን ካለው የኢትዮጵያ ህዝብ ቁጥር ጋር ተመሳሳይ 30 ያህል ያስፈልጋሉ ይላሉ አቅሙ ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚመጥን ነው ወይ? የሚለው ጥያቄ ላይ ከመጣ የኛን ማዕከል የሚመስል እስከ ሰላሳ የሚሆን ማዕከል ያስፈልገዋል የሚሉት ተቋሙ በነፃ አገልግሎቱን ቢሰጥም በርካታ ወጪዎች ያሉበት በመሆኑ ድጋፍ ይፈልጋል ብለዋል፡፡
የልብ ቀዶ ህክምና አገልግሎቱ እየተሰጠ ያለው በድጋፍ ነው የህክምና መሳሪያ እጥረት ትልቁ ፈተና ሆኖብናልም ይላሉ፡፡
በኢትዮጵያ የልብ ህሙማን ህፃናት መርጃ ማዕከል በአሁኑ ሰዓት ከ7 ሺህ በላይ የልብ ቀዶ ህክምና ወረፋ የሚጠባበቁ ታካሚዎች መኖራቸው ተነግሯል፡፡
ባሉት ችግሮች ምክንያትም የሚሠራው ጥቂት መሆኑንና ባለፈው አመት ብቻ 1300አዲስ ታካሚዎችን ማዕከሉ ቢቀበልም የቀዶ ህክምና አገልግሎቱን ያገኙት ግን 634 መሆናቸውን ሰምተናል፡፡
ምህረት ስዩም
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comentarios