የካቲት 26 2017 - ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች፣ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የንግድ ስራ የሚሆን የሞባይል መተግበርያ መልማቱ ተነገረ
- sheger1021fm
- Mar 5
- 1 min read
ለጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች፣ ለአነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች የንግድ ስራ ማቀላጣፊያነት የሚሆን የሞባይል መተግበርያ መልማቱ ተነገረ፡፡
መተግበርያውን አልምቶ ወደ ስራ ያስገባው ብሩህ ማይንድስ ኮንሰልት የተሰኘ ተቋም ነው፡፡

'መንሽ' የሚል መጠሪያ ያለው ይህ መተግበርያ አሁን ላይ በሁለት ቋንቋ (በአማርኛ እና በእንግሊዘኛ) አገልግሎት እንደሚሰጥ እና በሌሎች ቋንቋዎች ደግሞ በቅርቡ እንደሚጀምር ተነግሯል፡፡
ጀማሪ ስራ ፈጣሪዎች አነስተኛና መካከለኛ አምራች ኢንተርፕራይዞች ወደ ስራ ከመግባታቸው በፊትና ከገቡም በኋላ የስልጠና እና የምክር አገልግሎችን ጨምሮ የተለያዩ አገልግሎቶችን ያገኛሉ ተብሏል፡፡
አገልግሎቱን ሲጠቀሙ የነፃና የክፍያ አገልግሎቶች እንዳሉት ሰምተናል፡፡

በተለይ ለስራ ጀማሪዎች እና አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞችን በባለሞያ ምክር በስልጠና ወቅታዊ የገበያ መረጃ እንዲሁም መነሻ አነስተኛ ብድር አገልግሎቶችን ከተለያዩ የገንዘብ ተቋማት ጋር በትብብር እንደሚሰራም ተነግሯል፡፡
የንግድ ስርዓአት በተበታተነና ደረጃውን ባልጠበቀ መልኩ በልገሳ ሲተገበር በመቆየቱ ዘርፉ ትርጉምያለው ውጤት እንዳያመጣ አድርጎታልም ተበሏል፡፡
በዘርፉ የሚስተዋሉ ችግሮችን ለመፍታተት ይህ መንሽ የተሰኘ መተግበራያ ግሩም መላ ሲባልለት ሰምተናል፡፡
መንሽ መተግበሪያን ከፕለይ እስቶር እና አፕ እስቶር በማውረድ የንግድ ስራ አገልግሎቶችን እና የገበያ ትስስሮችን ማግኘት ይቻላል ተብሏል፡፡
መንሽ መተግበሪያን ያበለፀገው ብሩህማይንድስ ኮንሰልት ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ብቻ ከ27ሺ በላይ ወጣቶችን አሰልጥኖ ወደ ስራ ማሰማራቱን ሰምተናል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments