top of page

የካቲት 26፣2016 - በተነሳ የእሳት አደጋ የ2 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት ደርሷል ተባለ


ትናንት ከሌሊቱ 8:08 ሰዓት ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ አንድ ሁለት ቁጥር አውቶቢስ ማዞሪያ አካባቢ አዲሱና ቤተሰቦቹ በተባለዉ ሆቴል ላይ በተነሳ የእሳት አደጋ የሁለት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት ደርሷል ተባለ።


ህይወታቸዉ ያለፈዉ እድሜያቸዉ 28 እና 30 ዓመት የተገመተ ወጣቶች ሲሆኑ በሆቴሉ አልጋ ተከራይተዉ ተኝተዉ የነበሩ መሆናቸው ተነግሯል።


የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር ሰባት የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪ ከሰላሳ ሁለት የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች ጋር የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋ ወደ ሌሎች የመኖሪያና ንግድ ቤቶች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርሰ መቆጣጠር ተችሏል ተብሏል።


አደጋዉ የደረሰበት ቦታ የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎችን የሚያስገባ በመሆኑ የአደጋ መቆጣጠር ስራውን አስቸጋሪ አድርጎታል።


በሌላ በኩልም ትላንት በለሚኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ ስምንት በአንድ ሬስቶራንት ላይ የጋዝ ሲሊንደር ፈንድቶ በተነሳ የእሳት አደጋ ሶስት ሰዎች ጉዳት ደርሷል።


ወንድሙ ሀይሉየሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Comments


bottom of page