top of page

የካቲት 25፣2016 - የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ ይሰጣል ተባለ

የማህፀን በር ካንሰር በሽታ መከላከያ ክትባት ከዛሬ ጀምሮ በዘመቻ ይሰጣል ተባለ፡፡

ይህን ያለው የጤና ሚኒስቴር ነው፡፡


ሚኒስትሯ ዶክተር መቅደስ ዳባ በኢትዮጵያ በዓመት በማህጸን በር ካንሰር ምክንያት ከ5 ሺህ በላይ ሴቶች ህይወታቸው ያጣሉ ብለዋል፡፡


እንዲሁም እድሜያቸው ከ14 ዓመት በላይ ከሆኑት ሴቶች ከአምስቱ አራቱ በህይወት ዘመናቸው ለማህፀን በር ካንሰር ተጋላጭ እንደሚሆኑም ተናግረዋል፡፡


የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት ከ2011 ዓ.ም እስከ አሁን ባሉት ጊዜያት በዓመት 2 ጊዜ በ6 ወር ልዩነት ሁለት ዶዝ ክትባት ሲሰጥ መቆየቱን ሚኒስትሯ አስታውሰዋል፡፡


አለማቀፍ ጥናቶች መሰረት በማድረግ አንድ ጊዜ በተከተቡት እና ሁለት ጊዜ በተከተቡት ልጆች መካከል የክትባቱ ውጤታማነት ሲታይ ተመጣጣኝ የሚባል የመከላከል አቅም በማሳየቱ፣ ከዚህ ዓመት ጀምሮ አንድ ዶዝ ብቻ ይሰጣል ብለዋል፡፡በ2016 ዓ.ም 1.5 ሚሊዮን የሚጠጉ እድሜያችው 14 ዓመት የሆናቸው ሴቶች ልጆች ለመከተብ ታቅዷል ተብሏል።


ክትባቱ በትምህርት ቤቶች፣ በጤና ተቋማት፣ በግዝያዊ ክትባት መስጫ ጣቢያዎችም እንደሚሰጥ ሰምተናል።


ወላጆች ወይም አሳዳጊዎች እድሜያቸው 14 ዓመት የሆናቸው ሴት ልጆች የማህፀን በር ካንሰር መከላከያ ክትባት እንዲወስዱ በማድረግ ግዴታቸውን እንዲወጡም በጤና ሚኒስቴር ጥሪ ቀርቧል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


bottom of page