top of page

የካቲት  25፣2016 -ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ የግብርና ምርቶቿን የምትሸጣቸው ተፈጥሯዊ ባልሆኑት ዋጋ ነው ተባለ


 ኢትዮጵያ ምንም አይነት ሠው ሰራሽ ግብአቶች ያልተጨመሩባቸው ተፈጥሯዊ የግብርና ምርቶች ባለቤት መሆኗ ተደጋግሞ ይነገራል።

 

የጫካ ቡና እና የጫካ ማር ከእነዚህ ተፈጥሯዊ ምርቶች መካከል የሚጠቀሱ ናቸው።

 

እነዚህ ምርቶች በገዥዎች ዘንድ ከፍ ያለ ተፈላጊነት ስላላቸው ዋጋቸው ተፈጥሯዊ ካልሆኑት የተሻለ እንደሆነ ይነገራል።

 

ኢትዮጵያ ግን ምርቶቹን የምትሸጣቸው ተፈጥሯዊ ባልሆኑት ዋጋ እንደሆነ ሠምተናል።


የዚህ ምክንያቱ ደግሞ ምርቶቹ ምንም አይነት ሰው ሰራሽ ግብአቶች ያልተጨመረባቸው ወይም ተፈጥሯዊ ስለመሆናቸው የሚያረጋግጥ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

ይህንን የነገሩን በኢትዮጵያ ደረጃዎች ኢንስቲትዩት የደረጃዎች ዝግጅት መሪ ስራ አስፈጻሚ አቶ ይልማ መንግስቱ ናቸው።

 ተፈጥሯዊ የሆኑት የግብርና ምርቶች ‘’ከእርሻ ወደ ጉርሻ’’ የሚባሉ አይነቶች አይደሉም የሚሉት ስራ አስፈጻሚው፤ ብዙ ሂደቶችን እና በግብይት ሠንሰለቱ ውስጥ ያሉ ግለሰቦችን የሚነካ እንደሆነ ተናግረዋል።

‘’አለም አሁን ላይ እየፈለገ ያለው ተፈጥሯዊ የግብርና ምርቶች ነው፤ እኛም ስለ ምርቶቹ አጠቃላይ መረጃ የመስጠት አቅማችንን አሳድገን ከዚህ በበለጠ ለመጠቀም መስራት አለብን’’ ሲሉ አቶ ይልማ አስረድተዋል።

 


በዚሁ ጉዳይ ላይ አስተያየት የጠየቅናቸው የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ፤ የተባለው ጉዳይ እውነት መሆኑ ላይ ይስማማሉ፣ ‘’ምርቶቹ በትክክልም ተፈጥሯዊ ናቸው ወይ የሚለውን ማስተዋወቅ እና ለዚያ ማረጋገጫ እንዲሰጥ ማድረግ ግን፤ የአምራቾች እና በንግድ ሂደቱ ውስጥ የሚሳተፉ የተለያዩ ተቋማት ሃላፊነት ነው’’ ብለዋል።


የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን  ከተቋቋመ ገና ሁለት ዓመት እንኳን እንዳልሞላው የተናገሩት አምባሳደር ድሪባ

‘’እንዲያም ሆኖ ግን ወደ ውጪ የሚላኩ የግብርና ምርቶች እንደተባሉት ስለመሆናቸው በተቻለን መጠን የማረጋገጥ ስራ እንሰራለን’’ ብለውናል።

ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የሚያረጋግጠው ወደ ውጪ የሚላኩትን የግብርና ምርቶች ደረጃ ብቻ ሳይሆን፤ በሀገር ውስጥ ለፍጆታ የሚውሉትንም እንደሆነ አምበሳደር ድሪባ ተናግረዋል፡፡

 


ሰው ሰራሽ ግብአቶቸ የተጨመሩባቸው የግብርና ምርቶችን ለአለም ገበያ የሚያቀርቡ በርከት ያሉ ሀገራት ቢኖሩም እንደ ኢትዮጵያ ተፈጥሯዊ የሆኑ ምርቶችን ለአለም ገበያ የሚያቀርቡ ግን በቁጥር አነስተኛ እንደሆኑ ነው የሰማነው።

 

ንጋቱ ረጋሳ

 


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

 

 

 

Comentarios


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page