የአሜሪካ መንግስት የተራድኦ ድርጅት ( #USAID ) የሚሰጠውን ድጋፍ ማቆሙን ተከትሎ መንግስት ለተረጂዎች ለመድረስ የሚያስችለውን አፋጣኝ እርምጃ እንዲወስድ ተጠየቀ፡፡
በ8 ክልሎች ውስጥ ያሉ ከ4.5 ሚሊየን በላይ ኢትዮጵያውን የዩኤስ አይ ዲን የእለት ደራሽ እርዳታ ጠባቂ ናቸው፡፡
እነዚህን እርዳታ ፈላጊዎች ለመድረስ ባለው ዓመት ብቻ 150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ማድረጉን ዩኤስ ኤ አይዲ መረጃ ያሳያል፡፡
በዚህ ሁኔታ ድርጅቱ የማስተንቀቂያ ጊዜ እንኳን ሳይሰጥ በድንገት የምሰጠውን ድጋፍ አቁሚያለሁ ማለቱ አስደንጋጭ እንደሆነ የነገሩን የኢትዮጵያ የሲቪል ማህበራት ድርጅቶች ህብረት ለምርጫ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ አበራ ሃይለማሪያም፤ እነዚህን የእለት ድጋፍ ጠባቂ ሰዎችን ለመታደግ መንግስት ቅድሚያ ሰጥቶ መስራት አለበት ብለዋል፡፡
ለጊዜው ተፈጠረውን ክፍተት ለመሸፈን ሌሎች ለጋሽ ሃገራት የሚሰጡትን ድጋፍ እንዲጨምሩ ማግባባት እንደሚገባም አንስተዋል፡፡

በዩኤስ አይዲ ድንገተኛ ውሳኔ ምክንት ከ85 በላይ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ስራ ማቆማቸውን መረጃዎች ያመለክታሉ፡፡
አቶ አበራ እንደሚሉት በኢትዮጵያ ካሉ የሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ከ85 በመቶ በላዩ በዩኤስ አይዲ ጥገኛ ናቸው፤ ድጋፉ በመቆሙ የቤት ኪራይ፣ የሰራተኛ ደሞዝ ጭምር መክፈል እንዳቃታቸው እየተመለከትን ነው ይላሉ፡፡
ለአፋጣኝ መፍትሄ የሌሎችን ሃገራት ድጋፍ መጠየቅ ይገባል፤ለዘለቄታው ግን ድርጅቶቹ የገሀቢ መሰረታቸውን በሃገር ውስጥ ሃብት ስለማድረግ ማሰብ አለባቸው ሲሉም አስረድተዋል፡፡
ድርጅቱ ድጋፉን በማቆሙ 120 ሃገራት የዚህ ችግር ሰለባ ናቸው ተብሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ… https://tinyurl.com/5axktpe6
ምንታምር ፀጋው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comentarios