የካቲት 24 2017 - ሰው ሰራሽ አስተውሎት አሁን በሁሉም ዘርፎች በሚባል ደረጃ እየተተገበረ ነው
- sheger1021fm
- Mar 4
- 1 min read
ሰው ሰራሽ አስተውሎት ( #Artificial_Intelligence ) አሁን በሁሉም ዘርፎች በሚባል ደረጃ እየተተገበረ ነው፡፡
ቴክኖሎጂው ለሰው ልጅ ስጋትም እድልም ይዞ መጥቷል፡፡
በህክምና፣ በአውቶሞቲቭ ኢንዱስትሪው፣ በትምህርት ዘርፍ አለፍ ሲልም በእጃችን በማይለየው ስልካችም ጭምር ይህ ቴክኖሎጂ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡
አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ ተማሪዎች በቀላሉ የፈለጉትን መረጃ ለመረዳት ሲፈልጉ ያለ መምህር እውቀት እንዲሸምቱ በፅሁፍም በምስልም አቀናብሮ ይሰጣል፡፡
ታዲያ ይህ የሚሰጠው መረጃ እውነተኛም እንዳለው ሁሉ ሀሰት የሆነ መረጃ ሊኖረው እንደሚችል ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
የዘርፉ ምሁራን እንደሚሉት አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂን መግፋት አሁን ላይ አይቻልም እያሉ ሲሆን ከዚህ ይልቅ ሁነኛው መፍትሄ አሰራሮችና ህጎችን በመዘርጋት ትውልዱ በበጎ ጎን እንዲጠቅም ማድረግ ይሻላል ሲሉ ይደመጣል፡፡
ይህን ቴክኖሎጂ እንዴት እንጠቀመው? ጉዳቱስ በምን መንገድ እንቀንሰዋለን? ባለሙያዎችን አነጋግረናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
በረከት አካሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
ความคิดเห็น