top of page

የካቲት 22፣2016 - አበባ አልሚዎች የሚልኩት ምርት ‘’የእሳት እራት’’ ከሚባለው አይነት ተባይ ነፃ ስለመሆኑ እንዲያረጋግጡ ማሳሰቢያ ተሰጠ

በኢትዮጵያ የሚገኙ አበባ አልሚዎች ወደ አውሮፓ ህብረት የሚልኩት ምርት ‘’የእሳት እራት’’ ከሚባለው አይነት ተባይ ነፃ ስለመሆኑ በጥንቃቄ እንዲያረጋግጡ ማሳሰቢያ ተሰጠ።


ህብረቱ በተደጋጋሚ ተባዩን ከኢትዮጵያ በሚላክለት አበባ ውስጥ ካገኘ፤ ዕገዳ ሊጥል ይችላል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን አበባ ያዘጋጀውና አበባ አምራችና ላኪዎች ሊያደርጉት በሚገባ የጥንቃቄ እርምጃ ዙሪያ ያተኮረ ውይይት ተካሂዷል።


በእንግሊዝኛው ምህጻረ ቃል ኤፍ ሲ ኤም(FMC) የተባለው ተባይ፤ የቢራቢሮ ዝርያ ያለው እና በእኛ ሀገር የእሳት እራት እንደሚሰኝ የኢትዮጵያ ግብርና ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር አምባሳደር ድሪባ ኩማ ተናግረዋል።


ወደ አውሮፓ ሲሄድ ግን በአየር ንብረት ምክንያት ባህሪውን ይቀይራል ብለዋል።ተባዩ አውሮፓ ሲገባ ከመቶ በላይ የእጽዋት ዝርዋያዎችን እንደሚበላ የነገሩን ደግሞ የባለስልጣኑ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ወንዳለ ሃብታሙ ናቸው።


ተባዩ የዛሬ ሁለት አመት በኢትዮጵያ በሚገኙ የተለያዩ የአበባ እርሻዎች ላይ መገኘቱን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ አምባሳደር ድሪባ ኩማ በበኩላቸው፤ ይህን ተከትሎ ከሚላከው ናሙና ላይ ተባዩ ስለመኖር አለመኖሩ ለማወቅ የሚደረገው ምርመራ በህብረቱ ከፍ ማለቱን ጠቅሰዋል።


ከሚላከው ምርት ምርመራ የሚደረግበት የናሙና መጠን ወደ 25 በመቶ ከፍ እንዲል ህብረቱ መወሰኑን የተናገሩት ዋና ዳይሬክተሩ፤ የኢትዮጵያ አበባ ላኪዎች በዚህ ውስጥ በቶሎ ማስተካከያ ካላደረጉ ነገሮች ይበልጥ እየከበዱ እንደሚሄዱ አስረድዋተል፡፡


ህብረቱ የአንዳንድ አበባ ላኪ ሀገራት ምርት ሙሉ ለሙሉ እንዲመረመር መወሰኑን፤ የተናገሩት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ወንዳለ ሃብታሙ ደግሞለኢትዮጵያም ይሄ ከተወሰነ በጣም አስቸጋሪ ይሆናል ብለዋል፡፡


ኢትዮጵያውያን አበባ ላኪዎች ተባዩን በምን መንገድ ከእርሻቸው ማስወገድ ይችላሉ ያልናቸው አቶ ወንዳለ ተከታዩን መልሰዋል።


የእሳት እራት የሚባለው አይነት ተባይ አሁን ላይ የተገኘው ከ36 የአበባ እርሻዎች በሰባቱ እንደሆነ ሠምተናል።


ንጋቱ ረጋሣ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…Comments


bottom of page