top of page

የካቲት 21፣2016 - የዓድዋ ድል አፍሪካዊያን ወታደራዊ ሳይንስ አዋቂ መሆናቸውን ለአለም ያሳየ ድል ነው ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Feb 29, 2024
  • 1 min read

ይህን ያሉት ሌተናል ጀነራል አለምሸት ደግፌ የጦር ሀይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም አማካሪና ተኩስ አመራር ሀላፊ ናቸው፡፡


128ኛዉን የአድዋ የድል በዓል ምክንያት በማድረግ ''አድዋ የህብረ ብሔራዊነት ድምቀት የአንድነት ውጤት'' በሚል መሪ ሃሳብ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በራስ መኮንን አዳራሽ ውይይት አካሂዷል።


ለዉይይት የሚሆን የመነሻ ጽሁፍ ሌተናል ጄኔራል አለምሸት ደግፌ፣ የጥንታዊ ኢትዮጵያ አርበኞች ማህበር ፕሬዝዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ እና ፕሮፌሰር አየለ በክሪ አቅረርበዋል።


የአድዋ የድል በዓል አፍሪካዊያን ከነጮች እኩል የጦርነት ሳይንስ እንደሚያውቁ ያረጋገጠ እንደነበር ጀነራሉ አስረድተዋል።



የድል በዓሉን የምናከብርበት ዋነኛ ምክንያትም ኢትዮጵያ እንደ ሀገር እንድትቀጥል ያደረገ ስለሆነ ነው ብለዋል ጄኔራል አለምሽት።


ለመላው ጥቁር ህዝብ ቀና ማለት ምክንያት የሆነው የአድዋ ድልን በሀገር ጉዳይም አንድ ለመሆን መጠቀም ደግሞ የአሁኑ ትውልድ ሃላፊነት ነው ብለዋል።


ያሬድ እንዳሻው



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page