የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሃይ ሽፈራሁ እና የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል በተገኙበት በተሰጠ መግለጫ ላይ ነው የድረሻ ግዢው ወሬ የተሰማው፡፡
የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው ባንኩ ለካፒታል ገበያ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ራሱን የቻለ የፕሮጀክት ቢሮ ማቋቋሙን አስረድተዋል፡፡
በዚህም የተለያዩ ጥናቶችን በማድረግ አስፈላጊ የሆኑ ቅድመ ሁኔታዎችን ሲያመቻች ቆይቷል ብለዋል፡፡
የፕሮጀክቱ ቢሮ ዋና ዓላማ በካፒታል ገበያ ማቋቋሚያ ድንጋጌ መሠረት ስለካፒታል ገበያው ተዋናዮች፣ ተዛማች ፖሊሲዎች ዙሪያና በካፒታል ገበያ ኦፕሬሽን ዘርፎች ላይ አስፈላጊ ጥናት በማድረግና ፍኖታ ካርታ በማዘጋጀት ባንኩን በዘርፉ ስኬታማ እንዲሆን ማስቻል ነው ሲሉ ስረ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡
የኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገበያ የአክሲዮኑ አባል እንዲሆኑ ቅድሚያ ከተሰጣቸው ዘርፎች መካከል የፋይናንስ ተቋማት የመጀመርያ ረድፍ መያዛቸወን የገባያው ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል አስረድተዋል፡፡
አዋሽ ባንከ የ70 ሚሊዮ ብር አክሲዮን መግዛቱ ኩባንያው ሙሉ በሙሉ ካፒታሉን ተደራጅቶ ስራ እንዲጀምር ያስችለዋል ሲሉም ዶ/ር ጥላሁን ጠቅሰዋል፡፡
አዋሽ ባንክ ከኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ ስር ካሉት አራት ተቋማት ፣ከዘመን ፣ከግሎባል እና ሲንቄ ባንኮች ቀጥሎ ከሰነድ ሙዓለ ንዋይ ገባያ አክሲዮን የገዛ ባንክ ሆኗል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comentarios