በተለያዩ ኢትዮጵያ አካባቢዎች ያሉ ጦርነቶች፣ ግጭቶች እና አለመረጋጋቶች ነጋዴው ስራውን ተንቀሳቅሶ ለመስራት እንዳይችል አድርጎታል፡፡
ለንግድም ሆነ ለማንኛውም ስራ ሰላም መሰረት ቢሆንም በኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች ያሉ አለመረጋጋቶች እና ግጭቶች ግን ነጋዴው ለበርካታ ዓመታት ለፍቶ ያፈራውን ንብረት በቅጽበት እየወደመበት ነው ተብሏል፡፡
የኦሮሚያ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አቶ መገርሣ ረጋሣ ያለ ሰላም ንግድን ማሰብ አስቸጋሪ እንደሆነ በማስረዳት አሁን በኢትዮጵያ ያለው አለመረጋጋትም ለነጋዴው እንቅፋት ሆኗል ብለዋል፡፡
እሰራለው፣ እነግዳለው፣ አተርፋለው፣ እኖራለው የሚባለው ሰላም ሲኖር ነው ያሉት አቶ መገርሳ ሰላም በሌለበት ንግድ የለም ሲሉ አስረድተዋል፡፡
ለንግድ መሰረቱ ሰላም እንደሆነ የተናገሩት የኦሮሚያ ክልል ንግድ እና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት አሁን ያለው የሰላም እጦቱ ተንቀሳቅሶ ለመስራት እንቅፋት ሆኗል፣ ለነጋዴውም ስጋት ሆኗል ሲሉ ተናግረዋል፡፡
አቶ ተካ ወግአየው የተባሉ ነጋዴ ሰላም ባለመኖሩ ነጋዴው ለዓመታት ለፍቶ ያገኘው ንብረቱ በሰከንድ እየጠፋ ነው ብለዋል፡፡
የፋይናስ እና ኢንቨስትመንት መምህሩ ሰውአለ አባተ(ዶ/ር) ለንግድ ስራ ሰላም መሰረት እንደሆነ በመጠቆም ምርትን አንቀሳቅሶ ለመሸጥም ሆነ ለመግዛት አስፈላጊ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
አሁን በሀገሪቱ አለመረጋጋት ምክንያት የሆኑ ችግሮችን በንግግር መፍታት፣ ነጋዴው ተንቀሳቅሶ እንዲሰራ የተቀዛቀዘው ንግድ ወደቦታው እንዲመለስ እና ለሀገርም ለህዝብም እንዲበጅ ይረዳል ተብሏል፡፡
መንግስት በበኩሉ በሀገሪቱ ያለውን የሰላም እጦት ችግር በንግግር ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው እና የሰላም ጥሪዎችን ማቀርቡን ሲናገር ይደመጣል፡፡
ግን ችግሩ አሁንም የሰላማዊ ሰው ሕይወት እየነጠቀ፣ አካል እያጎደለ ንብረት እየወደመ ቀጥሏል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments