የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን ታህሳስ ወር ላይ ከተልኳቸው ውጪ ተንቀሳቅሰዋል በሚል በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የታገዱት የመብት ተሟጋች ተቋማት ጉዳይ በህግ አግባብ ብቻ ጉዳያቸው እንዲታይ ማሳሰቡን ተናግሯል፡፡
#የኢትዮጵያ_ሰብአዊ_መብቶች_ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆነው በቅርቡ የተሾሙት ኮሚሽነር ብርሃኑ አዴሎ በሲቪል ማህበረሰብ ድርጅቶች ባለስልጣን የታገዱት የመብት ተሟጋች ተቋማት ጉዳይ በህግ አግባብ ብቻ እንዲታይ ከባለስልጣን መስሪያ ቤቱ የስራ ኃላፊዎች ጋር መምከራቸውን ነግረውናል፡፡
የካቲት 17/2017 ዓ.ም ከባለስልጣን ማሰሪያ ቤት የስራ ሃላፊዎች ጋር መምከራቸውን የተናገሩት ኮሚሽነር ብርሃኑ በዚህም በሲቪል ማህበረሰብ ባለስልጣን የታገዱት የመብት ተሟጋች ተቋማት ጉዳያቸው ህግን ተከትሎ መፍትሔ እንዲገኝ ሃሳብ መስጠታቸውን ተናግረዋል፡፡
በዚህም ከባለስልጣኑ የስራ ሃላፊዎች ጋርም መግባባት ላይ መድረሳቸውን ጠቁመዋል፡፡
ኢሰመኮ በዛሬው እለትም በሰብአዊ ማብቶች ላይ ከሚሰሩ መንግስታዊ ካልሆኑ የመብት ተሟጋች ተቋማት ጋር እንደሚወያይ ተናግሯል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments