የካቲት 20፣2016 - ግሎባል ባንክ ከኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የ50 ሚሊዮን ብር ድርሻ መግዛቱ ተሰማ
- sheger1021fm
- Feb 28, 2024
- 1 min read
ግሎባል ባንክ ከኢትዮጵያ የሰነድ ሙዓለ ነዋይ ገበያ የ50 ሚሊዮን ብር ድርሻ መግዛቱ ተሰማ፡፡
ባንኩ ከዘመንና ሲንቄ ባንክ ቀጥሎ የ50 ሚሊዮን ድርሻ በመግዛት ሶስተኛው ባንክ ሆኗል፡፡
የካፒታል ገበያ በኢትዮጵያ ስራ መጀመሩን ተከትሎ የፋይናንስ ተቋሞች ከሰነድ ሙዓለ ነዋይ ገበያ ድርሻ መግዛታቸው በኢትዮጵያ የተጀመረውን የካፒታል ገበያ ወደፊት እያበረታው ነው ተብሏል፡፡
የኢትዮጵያ የሰነድ መዋዕለ ነዋይ ገበያ ዋና ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ጥላሁን እስማኤል ባንኮች ገበያውን እየተቀላቀሉ መሆኑ በጎ ተግባር ነው ብለዋል።
የግሎባል ባንክ ፕሬዘደንት ተስፋዬ ቦሩ ባንኩ ከኢትዮጵያ ሰነደ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ላይ የ 5 በመቶ አክስዮን በመግዛቱ ና በኢትዮዽያ የካፒታል ገበያ ሂደት ላይ መሳተፉን እውቅና ሰጥተዋል።
ከዚህ ቀደም ኢትዮ ቴሌኮም፣ የኢትዮጵያ ባህር ትራንስፖርትና ሎጀስቲክስ፣ የኢትዮጵያ መድን ድርጅት እንዲሁም ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት መስራች አባል መሆን የሚያስችላቸውን የ25 በመቶ ድርሻ ከኢትዮጵያ የሰነድ መዋለ ነዋይ ገበያ ገዝተዋል፡፡
ወሬውን የኢትዮጵያ የሰነዶች ሙዓለ ንዋይ ገበያ ለሸገር ነግሯል፡፡
ተህቦ ንጉሴ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments