top of page

የካቲት 20፣2016 - የሽንኩርት፣ የቃሪያ እና የቲማቲም ምርትን ያሳድጋሉ የተባሉ ምርጥ ዘሮች ከኔዘላንድስ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ተሰጡ

  • sheger1021fm
  • Feb 28, 2024
  • 1 min read

የሽንኩርት፣ የቃሪያ እና የቲማቲም ምርትን ያሳድጋሉ የተባሉ ምርጥ ዘሮች ከኔዘላንድስ ለኢትዮጵያ ገበሬዎች ተሰጡ፡፡


የአትክልት ዘሩን እርዳታ የሚሰጠው ቢ ኤ ኤስ ኤፍ(BASF) የተባለ ድርጅት ሲሆን የኔዘርላንድስ ልማት ድርርጅት ኤስኤንቪ(SNV) እርዳታውን ለገበሬዎች ያደርሳል ተብሏል፡፡


ለገበሬዎች ይሰጣል የተባለው የአትክልት ምርጥ ዘር 291 ሄክታር መሬት ይሸፍናል የተባለ ሲሆን በጦርነትና ድርቅ ውስጥ ያሉ ገበሬዎች ስራቸው እንዲቀጥሉ ያደርጋል ተብሏል፡፡


የቢ ኤ ኤስ ኤፍ የኢትዮጵያ ማኔጂንግ ዳይሬክተር ቤን ዴፕራቴር እንዳሉት አሁን ለገበሬዎች የሚሰጠው የአትክልት ምርጥ ዘር ገበሬዎቹ እራሳቸው እንዲችሉና የተሻለ ገበያ እንዲገኙ ያግዛል ብለዋል፡፡


የኤስኤንቪ የኢትዮጵያ ዳይሬክተር ጁሊ ግርሃም አሁን የሚሠጠው እርዳታ በተለይም ጦርነትና ድርቅ ባለባቸው የአማራ እና ትግራይ ክልል ገበሬዎች ላይ ትኩረት እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡


ኤስኤንቪ በ147 ወረዳዎች ባሉት 2 ሺህ የአርሶ አደሮች የመስክ ትምህርት ቤቶች 80ሺ የሚጠጉ ገበሬዎች በአመት ተጠቃሚ ያደርጋል ብለዋል፡፡


የግብርና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴዕታ መለስ መኮንን እንዳሉት በሁለቱ ክልሎች ውስጥ ድጋፍ የሚደረግላቸው 4 ሺህ ገበሬዎች ተለይተዋል ብለዋል፡፡


ቢ ኤ ኤስ ኤፍ ድጋፍ ያደረገው 800 ኪሎ ግራም ሽንኩርት፣ 666,000 ኪሎ ግራም ቃርያ እና 1.5 ሚልዮን ኪሎ ግራም ቲማቲም መሆኑን ሰምተናል፡፡


በረከት አካሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page