top of page

የካቲት 20፣2016 - በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች እርዳታ ጠባቂ ለሆኑ ለመጪው አንድ ዓመት እርዳታ ለማቅረብ 3.24 ቢሊዮን ያስፈልጋል ተባለ

በኢትዮጵያ በተፈጥሮ እና ሰው ሰራሽ አደጋዎች እርዳታ ጠባቂ ለሆኑ ሰዎች ለመጪው አንድ ዓመት የሰብዓዊ እርዳታ ለማቅረብ 3.24 ቢሊዮን ያስፈልጋል ተባለ።


እርዳታ ጠባቂ ለመሆን የተገደዱት ሰዎች ብዛት 21.4 ሚሊዮን ነው የተባለ ሲሆን የሚፈለገው ገንዘብ ከተገኘ 15.5 ሚሊዮን ሰዎች ድጋፍ ይደረግላቸዋል ተብሏል።


ሪፖርቱን ይፋ ያደረገው ዩኤን ኦቻ ከሚያስፈልገው 3.24 ቢሊዮን ዶላር ውስጥ 1.54 ቢሊዮን ዶላሩ ለቀለብ መስፈሪያ የሚሆን ነው ብሏል።


ድርቅ፣ ጎርፍ እንዲሁም ጦርነት በኢትዮጵያ ሚሊዮኖችን ለእርዳታ ጠባቂነት ዳርገዋቸዋል።



ንጋቱ ሙሉ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Commentaires


bottom of page