top of page

የካቲት 19 2017 - '' የወደቁትን አንሱ የበጎ አድራጎት ማህበር ተቋማትና ግለሰቦች እንዲያግዙት ጠየቀ ''

ከ800 በላይ አረጋዊያንን እየደገፈ የሚገኘው የወደቁትን አንሱ የበጎ አድራጎት ማህበር ተቋማትና ግለሰቦች እንዲያግዙት ጠየቀ፡፡


ከተቋቋመ 27 ዓመት የሞላው ይህ ማዕከል 90 በመቶ የሚሆኑት እናቶችና አባቶች መሆናቸውን ነግሮናል፡፡


#የወደቁትን_አንሱ የበጎ አድራጎት ማህበር ጠዋሪ ቀባሪ የሌላቸውን አረጋውያን ወደ ማዕከሉ በማስገባት የምግብ የጤናና ሌሎች አገልግሎቶችን እንደሚሰጣቸው ሰምተናል፡፡


ቋሚ ገቢ የሌለው ማህበሩ 200 በማዕከሉ 160 ደግሞ በተመላላሽ ከ 400 በላይ የሚሆኑትን ደግሞ ቤት ለቤት በአጠቃላይ ከስምንት መቶ በላይ አረጋዊያን በስሩ እንዳሉ ተናግሯል፡፡


በቀን በትንሹ ለአንድ ሰው ከ3,000 ብር በላይ ወጪ እንደሚያወጣ በማህበሩ የሃብት ማሰባሰብና የኮሙኒኬሽን ክፍል ዋና ሃላፊ ወ/ሮ አይናለም ሀይሌ ነግረውናል፡፡


በኢትዮጵያ የተለያዩ የግልም ይሁን የመንግስት ተቋማት የበጀታቸው አንድ አካል እንዲያደርጉ እንፈልጋለን ሲሉም ጠይቀዋል፡፡


ማህበሩ ከየካቲት 1 ጀምሮ እስከ 30 የወደቁትን አንሱ በሚል ኢትዮ ቴሌኮም የሰጠንን እድል በመጠቀም እንድታግዙን እንፈልጋለን ብለዋል፡፡


ይህም የኢትዮ ቴሌኮምን የማህበራዊ ትስስር ገጾችን ሲከተሉ ለሌሎች ሲያጋሩ ከ40 እስከ 30 ብር ለማህበሩ ገቢ እንደሚያደርጉ ከማህበሩ ሰምተናል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….




ማርታ በቀለ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page