የኢትዮጵያ ማዕከላዊ ስታቲስቲክስ በ2013 ዓ. ም ባወጣው መረጃ መሰረት ኢትዮዽያ 70.2 ሚሊዮን የዳልጋ ከብት፣ 42.9 ሚሊዮን በጎች፣ 52.5 ሚሊዮን ፍየሎች እና 8.1 ሚሊዮን ግመሎች አሏት፡፡
ይህ ቢሆንም ከዘርፉ እያገኘች ያለቸው ገቢ ካላት የእንስሳት ሀብት ብዛትና ከያዘችው ደረጃ ጋር አይመጣጠንም፡፡
የኮንትሮባንድና ህገ-ወጥ የቁም እንስሳት ወጪ ንግድ ህጋዊ ላኪዎችን እያማረረ መሆኑንም የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር በተደጋጋሚ ተናግሯል።
በዘርፉ ሲያጋጠሙ የነበሩ ችግሮችም ኢትዮጵያ በእንስሳት ብዛት በአፍሪካ ቀዳሚ 70.3 ሚሊዮን የሚገመቱ የቀንድ ከብቶች፣ 95.4 ሚሊዮን በግና ፍየሎች እንዲሁም 8.1 ሚሊዮን ግመሎች መገኛ ብትሆንም ዘርፉ ለረጅም ጊዜ ከፍተኛ ፈተናዎች ሲገጥሙት ቆይቷል።
ከእነዚህም ችግሮች መካከል ቀንድ ከብቶች የት እንዳሉ ለመከታተል ያለው እጅ ማጠርና ልማዳዊ የእንስሳት መለያ ዘዴ አንደኛው መሆኑ ተሰምቷል።
ብዙውን ጊዜም የእንስሳትን ጤናን፣ እንቅስቃሴን እና ባለቤትነት ለመከታተል መንገዱ አሁንም አስቸጋሪ ነው ተብሏል።

ይህም የእንስሳት ሀብት አያያዝ ችግር በመሆኑ እንስሳትን ለበሽታ እና ለስርቆት አደጋ እንዲጋለጡ በማድረግ ኢትዮዽያ ለውጭ የምታቀርባቸው የቁም ከብቶች ላይ ከፍተኛ የጥራት ችግር በመፍጠር በአለም አቀፍ ገበያ እንዲወድቁ ያደርጋል ተብሏል።
ይህንና መሳይ ችግሮችን ለመፍታት ያግዛሉ የተባሉ የእንስሳት አያያዝን የሚያዘምን እና የሚገኙበት ቦታ በቀላሉ ለማወቅ የሚያስችል ዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን ወደ ኢኮኖሚው ማስገባቱን ኢትዮ ቴሌኮም ተናግሯል።
ይህ ዘመናዊ መፍትሄ ምርታማነትን ለማሳደግ፣ የእንስሳትን ደህንነት ለማሻሻል በተለይም የእንስሳት
ባለቤቶች የፋይናንስ አገልግሎት እንዲያገኙ በማድረግ የፋይናንስ ክፍተትን ለማጥበብ በብርቱ እንደሚያግዝ የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ተናግረዋል፡፡
አርሶ አደሮች እና እንሰሳት አርቢዎች ወጭ ንግድ ላኪዎች በቀላሉ እንስሳቶቻቸውን መከታተል፣ ያሉበትን ቦታ መለየት እና የጤና ሁኔታቸውን መገምገም እንዲችሉ አገልግሎቱ የሚያዋጣው አለው ተብሏል።
ኢትዮዽያ በኮንትሮባንድ ሰበብ በቁም ከብት የምታጣው ገቢ እንዲገታ እና ዘርፉ ለኢኮኖሚያዊ እድገት የተሻለውን እንዲያቀብል ይህ የዲጅታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ መፍትሄ ወደ አገልግሎት መግባቱን ሰምተናል።
ኩባንያው ዛሬ ወደ ኢኮኖሚው ያስገባው የዲጂታል ላይቭስቶክ ትራኪንግ ሶሉሽን ኢትዮጵያ ወደ ዘመናዊ እና ይበልጥ የቴክኖሎጂ ትስስር ወዳለው ግብርና እንድትገባ ያግዛታል ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ተናግረዋል።
ኩባንያው ከዚህ ባለፈ ሌሎች ስድስት የቴክኖሎጂ መፍትሄዎችን ይፋ አድርጓል።
ከነዚህም ውስጥ በእጅ ስልክ ቴሌ ፑሽ-ቱ-ቶክ/ቪዲዮ ወይም ዎኪ ቶኪ፣ ኮር ባንኪንግ ሶሉሽን፣ የትምህርት አመራር ስርዓት ሶሉሽን፣ የአንድ ቢሮ ትብብር እና ምርታማነት ሶሉሽን በተጨማሪም ለተለያዩ ኩባንያዎች መፍትሄ የሚያቀብሉ መፍትሄዎችን ይፋ አድርጓል።
ተህቦ ንጉሴ
Hi