top of page

የካቲት 19፣2016 - የእንቦጭ አረምን ከወዲሁ መከላከል ካልተቻለ ህዳሴ ግድቡ ጋር ሊሄድ ይችላል ሲል የብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ተናገረ

የጣናን ሐይቅ 24,000 ሄክታሩ የሸፈነው የእንቦጭ አረምን ከወዲሁ መከላከል ካልተቻለ ህዳሴ ግድቡ ጋር ሊሄድ ይችላል ሲል የብዝሃ ህይወት ኢንስቲትዩት ተናገረ።


የመጤ አረሙ ሽፋንም በሀገር አቀፍ ደረጃ እየጨመረና እየተስፋፋ እንደመጣ የተነገረ ሲሆን፤ ከጣና ሐይቅ ባለፈ ለቆቃ፣ ለባቱ እና ለሌሎች ሐይቆችም ስጋት መሆኑን ኢኒስቲትዩት እወቁት ብሏል።

በኢንስቲትዩቱ የጄኔቲክ ሀብት አርክቦት እና ጥቅም ተጋሪነት ምርምር መሪ ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር አብዮት ብርሃኑ በአማራ ክልል ያለው አለመረጋጋት መጤ አረሙ በአካባቢው እንዲሰፋፋ እና የመከላከል ስራው ችላ እንዲባል ምክንያት ሆኗል ብለዋል።


መጤ አረሙን ሁሉም የሚመለከታቸው አካላት በቅንጅት መከላከል ካልቻሉ ዛሬ ለልማት ተብለዉ እየተገነቡ ባሉ ግድቦች እና የመስኖ ፕሮጀክቶች ላይም ጉዳት ማድረሱ አይቀርም ተብሏል።


ዓሳን ጨምሮ በባህር ውስጥ ያሉ ብዝሃ ሕይወቶችን ማጥፋት፣ የውሃ ክምችትን ከመቀነስ እስከ ማጥፋት፣ የእርሻ እና የግጦሽ መሬት መውረር መጤ አረሙ ከሚያደርሳቸው ጉዳቶች ጥቂቶቹ ናቸው ተብሏል።ያሬድ እንዳሻው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…Comments


bottom of page