top of page

የካቲት 19፣2016 - ወረቀትና የወረቀት ውጤቶችን በተመለከተ ሲካሄድ የቆየው ጥናት ተጠናቋል ተባለ

  • sheger1021fm
  • Feb 27, 2024
  • 1 min read

በሀገር ውስጥ ሊመረቱ የሚችሉ ወረቀትና የወረቀት ውጤቶችን በተመለከተ ሲካሄድ የቆየው ጥናት ተጠናቋል ተባለ፡፡


በኢትዮጵያ ወረቀት እና የወረቀት ውጤቶችን የሚያመርቱ እንዲሁም የማሸግ እና ማተም አገልግሎቶች የሚሰጡ የተለያዩ ፋብሪካዎች አሉ።


የእነዚህ ፋብሪካዎች አቅም ግን በሀገር ውስጥ ካለው ፍላጎት ጋር ሲነሳሰር አነስተኛ እንደሆነ ተነግሯል፡፡


በዚህም ምክንያት ምርቶቹ በአብዛኛው ከውጪ ይገባሉ ሲሉ በኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የመሰረተ ልማት እና ግብአት ዘርፍ አማካሪ አቶ ዳንኤል ኦላኒ ነግረውናል።


ፍላጎቱን የሚሸፍን ወረቀት በሀገር ውስጥ እንዲመረት መንግስት ማሻሻያዎችን እንደሚያደርግ የተናገሩት አማካሪው፤ በዚህ ዙሪያ ያደረጋቸው አንዳንድ ጥናቶችም አልቀዋል ብለዋል፡፡


የፐልፕ፣ ወረቀትና ፓኬጅንግ አምራቾች ማህበር ከሠሞኑ እንደተመሰረተም ሠምተናል፡፡


የማህበሩ መመስረት መንግስት ዘርፉ እንዲሻሻል የሚያሰራውን ስራ ያግዛል ሲሉም አቶ ዳንኤል ተናግረዋል፡፡


ንጋቱ ረጋሣ



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page