በክልሉ ለስደተኞች የሰብአዊ አቅርቦት ተቋርጦ ስለነበር ለግጭት ምክንያት ሆኖ ነበር ተብሏል።
ከፌዴራል መንግስት እና ከዓለም አቀፍ ለጋሽ ድርጅቶች በመነጋገር እና በመወያየት ተቋርጦ የቆየው የሰብዓዊ አቅርቦት ችግር በመፈታቱ አንደኛው የግጭት መነሻ፤ መፍትሄ እንዳገኘ ክልሉ አስረድቷል።
በክልሉ የተጠለሉ ስደተኞች የሰብዓዊ አቅርቦቱ ሲቋረጥም ሆነ ሲዘገይ ወደ አካባቢው የአርሶ አደር ማሣ በመግባት እና ሌሎት ጥፋቶችን ሲፈጸሙ ነበረ ሲሉ የክልሉ የኮሚዩኒኬሽን ቢሮ ሃላፊ ኡጁሉ ጊሎ ነግረውናል።
የጋምቤላ ክልል ከደቡብ ሱዳን ተፈናቅለው የመጡ ከ385 ሺህ በላይ ስደተኞች ያሉበት ክልል ሲሆን ይህም ከፍተኛ ቁጥር ያለው ስደተኛ የሚኖርበት ክልል ያደርገዋል።
በተያያዘ ወሬ የኢትዮጵያ ስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡ ስደተኞችን እየተቀበለ እንዳለ አስረድተዋል።
ያሬድ እንዳሻው
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments