በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት የተዘጋጀው መፅሐፍ ለ1ኛ ደረጃ ተማሪዎች አንድ ለአንድ ሲደርስ ለቅድመ 1ኛ ደረጃ ተማሪዎች ደግሞ 1 መፅሐፍ ለ 4 ተማሪ እንዲጠቀሙ እየተደረገ ነው ተባለ፡፡
ቅድመ አንደኛ ደረጃ ላይ በ2015 ዓ.ም አዲሱ ስርዓተ ትምህርት ወደ ትግበራ የገባው በሙከራ ደረጃ እንደሆነ የተናገሩት የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ ወይዘሮ ታጋይቱ አባቡ በዚህም ምክንያት መፅሐፉ ገና በህትመት ላይ እንዳለ ለሸገር ተናግረዋል፡፡
ቅድመ አንደኛ ደረጃ ላይ ያሉ ተማሪዎች መፅሐፍቱን አንድ ባንድ እንዲያገኙ ለማድረግ ቢሮው ስራዎችን እየሰራ መሆኑን የተናገሩ ወይዘሮ ታጋይቱ ተማሪዎቹ በጨዋታ መልክ ትምህርቱን ለማስያዝ ስለሚሰራ መፅሐፍት አለማግኘታቸው ያን ያህል ክፍተት አይፈጥርም ብለዋል፡፡
በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተገኝተው የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በሰጡት አስተያየት፤ ለቅድመ አንደኛ ደረጃ ተማሪዎች 1 መጽሐፍ ለ9 ተማሪዎች፤ ለመጀመሪያ ደረጃ ተማሪዎች 1 መጽሐፍ ለ5 ተማሪዎች እና ለመካከለኛ ደረጃ ተማሪዎች 1 መጽሐፍ ለ4 ተማሪዎች እንዲዳረስ መደረጉን ተናግረው ነበር፡፡
ከ9ኛ እስከ 12ኛ ክፍል ተማሪዎችም በ45 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር የመማሪያ መፅሀፍትን ለማሳተም ኮንትራት ፈርሞ እያሳተመ በመሆኑ ከ22 ሚሊዮን በላይ የመማሪያ መጻሕፍት ታትመው ከ20 ሚሊዮን በላይ ለክልሎች መሰራጨቱን ተናግረዋል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments