top of page

የካቲት 18 2017 - ከኢትዮጵያ ህዝብ የጤና መድህን የሚጠቀመው ከ54,000,000 ተሻግሯል ተባለ፡፡

  • sheger1021fm
  • Feb 25
  • 1 min read

ከኢትዮጵያ ህዝብ የጤና መድህን የሚጠቀመው ከ54,000,000 ተሻግሯል ተባለ፡፡


ከተጠቃሚዎቹ የሚገኘው የአገልግሎት ክፍያም ለጤና ተቋማት የገቢ ምንጭ እየሆነ መጥቷል መባሉንም ሰምተናል፡፡


የተጠቃሚው ቁጥር እና የሚገኘው ገቢ በፍጥነት እየጨመረ መጥቷል ሲሉ የነገሩን #የኢትዮጵያ_ጤና_መድህን አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ተስፋዬ ወርቁ ናቸው፡፡


54 ሚሊዮን የተጠቃሚዎች ቁጥርም የተመዘገበው እስከ 2016 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ ሲሆን በዚህ ዓመት የተመዘገበው ሲጨመር ቁጥሩ ከዚህም ከፍ እንደሚል ጠቁመዋል፡፡


ለጤና መድህን አገልግሎት የሚከፈለውን ክፍያ መክፈል የማይችል ማንኛውም ሰው፤ መንግስት ወጪው ሸፍኖለት ከሌላው እኩል መታከም ይችላል ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ አስረድተዋል፡፡


ክልሎች እና ከተማ አስተዳደሮች መክፈል ለማይችሉት ድጎማ እንዲያደርጉ በህግ ይገደዳሉ ሲሉም ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ተስፋዬ ተናግረዋል፡፡

አሁን ካለው ከ54 ሚሊዮን በላይ ተጠቃሚው ወደ 12 ሚሊዮኑ ከመንግስት ተደጉሞለት በ #ነጻ የሚታከም ነውም ብለውናል፡፡


ከጤና መድህን የሚገኘው ገቢ ለህብረተሰቡ አግልግሎት ከመስጠት ባለፈ ለጤና ተቋማት ማሽኖች እና ሌሎች የህክምና መሳሪያዎችንም ለመግዛት እያገዘ ነው ሲሉ ነግረውናል፡፡


በ2015 ዓ.ም ከጤና መድህን ክፍያ 6 ቢሊዮን ብር ተገኝቶ እንደነበረና በ2016 ዓ.ም ደግሞ በእጥፍ አድጎ 12 ቢሊዮን ብር መድረሱን ሰምተናል፡፡


በጤና መድህን እና ከፍለው በሚታከሙት መካከል በአንዳንድ ተቋማት የሚስተናገዱበት ሁኔታ ይለያያል በሚል አንዳንዶች ስለሚያነሱት ቅሬታ የጠየቅናቸው አቶ ተስፋዬ እንዳንዴ መሰል ቅሬታዎች ይደርሱናል ለማረም እየሰራን ነው ብለውናል፡፡


በኢትዮጵያ የጤና መድህን አገልግሎት ከተጀመረ 13 ዓመት ሞልቶታል፡፡


ማንያዘዋል ጌታሁን

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page