ከ40 በላይ የደረሱት የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች፣ ቁጥራቸው የበዛ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት፣ የሞያና ቴክኒክ ማሰልጠኛዎች በየአመቱ በሺህዎች የሚቆጠሩ ወጣቶች ያስመርቃሉ።
መገልገያ ቁሳቁሱን፣ የሚበላ የሚጠጣውን ማምረት መስራት ደግሞ ከተመራቂዎቹ ከሚጠበቁት መካከል አንደኛው ነው፡፡
ግን ዛሬም የበዛው መገልገያ ቁሳቁስ ፣ ምግብ መጠጡም ከውጭ በገፍ ይገባል ለምን ስንልም የዘርፉን ባለሞያ ጠይቀናል፡፡
ፕሮፌሰር ዳንኤል ቅጣዉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ በኢንደስትሪያል ኢንጅነሪንግ ክፍል በማገልገል ላይ ይገኛሉ።
የመንግስት፣ የኢንዱስትሪዎች እና የከፍተኛ ተቋማት አለመተማመን መኖር ኢትዮጵያን የውጭ ምርትን ጠባቂ እንጂ አምራች እንድትሆን አላደረጋትም ሲሉ ይናገራሉ።
የሶስቱ አለመተማመን ኢትዮጵያ በተማሩ ልጆቿ ምርታማ እንዳትሆን አድርጓታል ብለዋል።
ፕሮፌሰር ዳንኤል በከፍተኛ ተቋማት ፣በኢንደስትሪዎችና በመንግስት መካከል ያለመተማመን ክፍተት አለ።
ለመሆኑ በዚሁ ምክንያት ኢትዮጵያ ምን አጣች? ተፅእኖውስ? ብለን ለፕሮፌሰር ዳንኤል ላነሳነው ጥያቄ ከጅምሩ ኢትዮጵያ ምን አላት እና ምን ታጣለች ሲሉም ነግረውናል።
በኢትዮጵያ ማምረት እየተቻለ ነገር ግን ከውጪ አሁንም ማሽነሪዎችን እያስገባን ነው የሚሉት ፕሮፌሰር ዳንኤል በአገር ውስጥ ለማምረት አሳሪ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት መንግስት ፖሊሲዎችን ማሻሻል እንዳለበትም ይናገራሉ።
ኢንዱስትሪዎችም ከከፍተኛ ተቋማት ጋር አብረው ሊሰሩ ይገባል ብለዋል።
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…
ፍቅሩ አምባቸው
Comments