አገልግሎቱ የተለያዩ የታሪክ መዛግብትን ላለፉት 80 ዓመታት ይዞ በማቆየት አንብቢያን እንዲያውቁት አድርጓል ተብሏል።
የኢትዮጵያ ቤተ መዛግብት እና ቤተ መፅሐፍት አገልግሎት ወይም ወመዘክር በ80 ዓመት እድሜው የተላያዩ ታሪካዊ መፅሀፍትና ድርሳናትን ይዞ መቆየቱን የተነገረ ሲሆን ትውልዱ ለንባብ እንዲተጋ አድርጌያለሁ ብሏል።
የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ቀጀላ መርዳሳ ‘’ወመዘክር ሀገሪቱ ያሏትን መንፈሳዊ፣ ቁሳዊ፣ ታሪካዊ እና ሀይማኖታዊ ትውፊቶችን ማሳያ የሆኑ ታሪክን ከትበው፣ ሁነትን መዝግበው የያዙ ሰነዶችና መፃህፍት’’ ይዟል ብለዋል።
‘’መንግስት አሁንም ለወመዝክር የሚያደርገውን ድጋፍ ይቀጥላል’’ ሲሉ ሰምተናቸዋል።
ወመዘክር ላይ የተለያዩ ምሁራን ጥናትና ምርምር ለማድረግ የተለያዩ መዛግብትን እንደሚጠቀሙ የተነገረ ሲሆን አሁንም ምሁራን በተቋሙ ጥናታቸውን እንዲያደርጉ ጥሪ ቀርቧል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments