top of page

የካቲት 16፣2016 - ከደሴ ሸዋሮቢት፣ ደ/ብረሀን የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቆመ መወሰኑ ተሰማ

ከደሴ፣ ሸዋሮቢት፣ ደ/ብረሀን እንዲሁም ከደ/ብረሀን፣ ሸዋሮቢትና ደሴ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ለጊዜው እንዲቆመ መወሰኑ ተሰማ።


ውሳኔው እወቁት ያለው የማዕከላዊ ሸዋ ኮማንድ ፖስት መሆኑን የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን አውርቷል፡፡

በዚህም መሰረት ከዛሬ ጀምሮ የትኛውም አይነት የትራንስፖርት አገልግሎት ከደሴ፣ ሸዋሮቢት፣ ደ/ብረሀን እንዲሁም ከደ/ብረሀን ሸዋሮቢትና ደሴ ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቆም ተብሏል፡፡

የትራንስፖርት ክልከላው የተላለፈው ኮማንድ ፖስቱ ‘’ፅንፈኛ ሀይሎች’’ ሲል የጠቀሳቸው ሃይሎች ላይ እርምጃ እየወሰደ በመሆኑ ሰላማዊ ዜጎች ጉዳት እንዳይደርስባቸው እና አካባቢውን በአጭር ቀናት ከፅንፈኛ ሀይሉ ነፃ ለማድረግ የኦፕሬሽን ስራ የተጀመረ ስለሆነ ነው ተብሏል፡፡


የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቆም የተወሰነ መሆኑ ታውቆ ህብረተሠቡ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ የፀጥታ ሀይሉም ውሳኔው ይፈፀም ዘንድ ክትትል እንዲያደርግ ኮማንድ ፖስቱ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡



የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

Comments


bottom of page