በመንገዳችሁም ይሁን እግር ጥሏችሁ በቸርችል ጎና ቁልቁል ወርዳችሁ ኢሚግሬሽንና የዜግነት አገልግሎት ጋር ስትደርሱ ቀን ሳይለይ በርካታ ወጣቶችን መታዘባችሁ አይቀርም፡፡
ሴቱም ወንዱም ከሀገር በገፍ ለመውጣት በሚመስል መልኩ የፓስፖርት ቀጠሮ ጠባቂው፣ ከኤጀንሲዎች ደጃፍ የሚመላለሰው ብዙ ነው፡፡
ፓስፖርትም፣ ኤጀንሲም ጋር ያልደረሱ በየበርሃው፣ በየባህሩ የሚጓዙትም ቁጥራቸው የበዛ መሆኑንን በየጊዜው የሚወጡ ሪፖርቶች ያሳያሉ፡፡፡
ፓስፖርት አውጥተው በቦሌ ለመሄድ የተሰናዱትን አነጋግረናል፡፡
መደበኛ ያልሆነው ጉዞስ እንዴት ነው? ስንልም የሚመለከተውን የመንግስት መ/ቤት ጠይቀናል፡፡
ፋሲካ ሙሉወርቅ
Comments