የካቲት 14 2017 - ''የጥናት እና ምርምር ስራዎች ቢኖሩም ጊዜ የላቸውም በሚል እንድንሳተፍ እድል አይሰጠንም''
- sheger1021fm
- Feb 21
- 1 min read
በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ የሚሰሩ ሴት ተመራማሪዎች ቁጥር ካለፈው ጊዜ የጨመረ ቢሆንም ከአጠቃላይ ቁጥሩ አንፃር ግን አሁንም በቂ አይደለም ተባለ፡፡
ከአራት ዓመት በፊት በተጠና ጥናት መሰረትም በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ያሉ ሴቶች 16.9 በመቶ መሆኑን ያሳያል፡፡
በሌላ በኩል ደግሞ አዳዲስ ሴት ተመራማሪዎችን ወደ መስመሩ ከማምጣት ባለፈም ያሉትም ቢሆን የሚገጥሟቸው ችግሮች ቀላል አለመሆናቸውን ጥናት አሳይቷል፡፡
ከጊዜ ወደ ጊዜ በዘርፉ የሴቶች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጥናት ያሳያል የተባለ ሲሆን አሁን ያለው ቁጥር ግን በቂ አይደለም፤ ያሉትም ቢሆን ብዙ ችግሮች ሲያጋጥሟቸው ቆይቷል ተብሏል፡፡
ተቋማት ብቻ ሳይሆኑ የስራ ባልሰደረቦችም የተሳሳተ አመለካከት አለ፤ ጥናት እና ምርምር ስራዎች ቢኖሩም ጊዜ የላቸውም በሚል እንድንሳተፍ እድል አይሰጠንም ይላሉ፡፡
ሴቶቹ ባሉበት ዘርፍ ወደፊት እንዳይመጡ እንቅፋት ከሆነባቸው ችግሮች መካከል ሌላኛው ደግሞ በተቋሙ ያለው መዋቅር ውስብስብ መሆኑ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡
ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ ….
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Commentaires