top of page

የካቲት 14 2017 - የአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያን ዓመታዊ ጥቅል ምርትበ10 በመቶ እየቀነሰው መሆኑ ተነግሯል

  • sheger1021fm
  • Feb 21
  • 2 min read

የአየር ንብረት ለውጥ የኢትዮጵያን ዓመታዊ ጥቅል ምርት ( #GDP ) በ10 በመቶ እየቀነሰው መሆኑ ተነግሯል፡፡


በዚህ ሳቢያ በሚደርስ የምርታማነት መቀነስ በአማካኝ በየዓመቱ 3 ሚሊዮን የሚደርሱ ኢትዮጵያውን ለምግብ እጥረት ይጋለጣሉ፤ በዚህም በተለይ ሴቶችና ህፃናት ይበልጥ ተጎጂ ናቸው ተብሏል፡፡


ይህ ተባለው ፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ የተባለው ተቋም አጋር ካላቸው ተቋማት ጋር በመሆን የአየር ንብረት ለውጥ በስርዓተ ምግብና በስርዓተ ፆታ ላይ እያስከተለ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት ይፋ በሆነበት ወቅት ነው፡፡


በቢልና ሚሊንዳ ጌትስ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ ለ3 ዓመታት የሚቆየው ፕሮጀክት ይፋ በተደረገበት መርሃ ግብር ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡት በኢትዮጵያ የምግብ ስርዓት ደህንነታቸው የተጠበቁና በምግብ ንጥረ ነገር የበለፀጉ ምግቦች ባለሙያ የሆኑት አቶ መሰረት ፀጋዬ፤ የአየር ጠባዩ መዛባት ተከታታይ የድርቅ አደጋዎችንም አስከትሏል፤ ለአብነትም ከ3 ዓመታት በፊት በዚህ ምክንያት በተከሰተው የድርቅ አደጋ በሰብልና በእንሰሳቱ ላይ የደረሰውን ውድመት እንኳን ብንመለከት ኢትዮጵያ በድርቁ ምክንያት 4.4 ቢሊዮን ዶላር ወይም በዚያን ወቅት በነበረው የምንዛሪ ስሌት 220 ቢሊዮን ብር እንዳጣች በዘርፉ የተደረገው ጥናት እንዳሳየ አቶ መሰረት ነግረውናል፡፡


ችግሩን የስርዓተ ምግብንና የስርዓተ ፆታን ጉዳይ ጋር በማስተሳሰር ለመስራት በማሰብ ፕሮጀክቱ እንደተጀመረ የነገሩን በፎረም ፎር ሶሻል ስተዲስ የፕሮጀክቱ የሞኒተሪንግና ኢቫሉዌሽን ኃላፊ የሆኑት ወ/ሮ ሰላም ኢሳያስ፤ ፕሮጀክቱ በ3 ዓመታት ጊዜ ቆይታው ከጉዳዩ ባለቤቶቨች ጋር ዙሪያ ውይይቶችን ያካሂዳል፣ጥናቶችንም ያደርጋል ብለውናል፡፡


በመንግስት የሚሰራው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ስራ ሊበረታ ይገባል የሚሉት የስርዓተ ምግብ ባለሙያው አቶ መሰረት ፀጋ፤ በገጠር ያሉ ሴቶችን እንግልት ለመቀነስ ብሎም የደን መጨፍጨርን ለመከላከል የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ዝርጋታው በተለይም የሶላር ኤነርጂን በየገጠሩ ማዳረስ ይገባልም ብለዋል፡፡


የአየር ንብረት ለውጡ የ10 በመቶ እንዲቀንስ አድርጎታል የተባለው የኢትዮጵያ ጂዲፒ 100 ቢሊዮን ዶላር ወይም 12.5 ትሪሊዮን ብር መድረሱን የገንዘብ ሚኒስቴር መረጃ ያሳያል፡፡


የገንዘብ ሚኒስቴር በቅርቡ ባወጣው የሩብ ዓመት አጠቃላይ የመንግሥት የዕዳ ሰነድ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከመደረጉ አንድ ወር በፊት ማለትም በሰኔ 2016 ዓ.ም የአገሪቱ አጠቃላይ የአገር ውስጥ ምርት ሲሰላ 207 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን፣ የውጭ ምንዛሪ ለውጡ ከተደረገ በኋላ በ2017 ዓ.ም መስከረም ወር መጨረሻ ላይ ወደ 100 ቢሊዮን ዶላር መውረዱን መናገሩ ይታወሳል፡፡


ምንታምር ፀጋው


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…


📌 Website: https://shorturl.at/yCz7q


📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd


📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s


📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il


Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page