በአዲስ አበባ ከተማ የሸቀጦች ዋጋ መናር የነዋሪውን ህይወት እንደፈተነው ተደጋግሞ ይነገራል።
ከቅርብ ጊዝ ወዲህ ጤፍን ጨምሮ ሌሎች ሸቀጦች በአንድ ጀንበር ዋጋቸው ከፍ ማለቱ የሚታወቅ ነው፡፡
ነገር ግን ከሰሞኑ የሽንኩርት እና የቲማቲም ዋጋ እቀነሰ ቢሆንም የጤፍ ዋጋ ጨምሯል፡፡
ጤፍ ከወራት በፊትም ከስድስት ሺህ ብር ወደ አስራ ሁለት ሺህ፣ አስራ ሶስት ሺህ እና አስራ አራት ሺህ ብር በአንድ ጊዜ የዋጋ ጭማሪ አሳይቷል።
ሸገር በአንዳንድ ወፍጮ ቤቶች ተዘዋውሮ ጤፍ ሲገበያይ የሰነበተበትን ዋጋ ተመልክቷል፡፡
በዚህም በየደረጃው ከ135 ብር እስከ 145 ብር በኪሎ እየተሸጠ መሆኑን አይቷል፡፡
እዚሁ በሀገር ቤት ተመርቶ የሚቀርበው ጤፍ ለምን በዚህ ልክ ተወደደ?
ለምንስ የአቅርቦት እና የፍላጎት አለመጣጣም ሊያጋጥም ቻለ?
ሸገር የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ንግድ ቢሮን ጠይቋል።
ፋሲካ ሙሉወርቅ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Yorumlar