top of page

የካቲት 13 2017 - በግል የውጭ ምንዛሪ እንዲሸጡ ፍቃድ ከብሔራዊ ባንክ ያገኙ የፎርኤክስ ቢሮዎች የውጭ ምንዛሪ አከማችተን ብንጠብቅም ባሰብነው ልክ እየሸጥን አይደለም አሉ።

በግል የውጭ ምንዛሪ እንዲሸጡ ፍቃድ ከብሔራዊ ባንክ ያገኙ የፎርኤክስ ቢሮዎች የውጭ ምንዛሪ አከማችተን ብንጠብቅም ባሰብነው ልክ እየሸጥን አይደለም አሉ።


ይህ የሆነበት ምክንያትም በተፈለገው መጠን የውጭ ምንዛሪ ስላለ እና በፍላጎት መጠንም ስለቀረበ ነው መባሉን ሰምተናል።


በአዲስ አበባ ከባንክ ውጭ የውጭ ምንዛሪ ሸያጭና ግዢ እንዲሰጡ ፍቃድ ከተሰጣቸው ቢሮዎች ምንም አይነት የውጭ ምንዛሪ እጥረት የለብንም ብለዋል።


ይህን መረጃ የነገሩን የኢትዮ ፎሬክስ የውጭ ምንዛሪ ቢሮና የዮጋ ፎሬክስ ቢሮ ናቸው።


አገልግሎት ሰጭዎቹ ወደ ስራ ከገቡ ስድስት ወር እንደሆናቸው ተናግረው በዚህ ጊዜ ውስጥ በየቀኑ ለብሔራዊ ባንክ ሪፖርት እንደሚልኩ አስረድተውናል።

በየቀኑም ለአንድ አገልግሎት ፈላጊ ከአምስት ሺህ እስከ ሰባት ሺህ ዶላር የውጭ ምንዛሪ እንደሚሸጡ ነግረውናል።


የኢትዮ ፎርኤክስ ስራ አስፈፃሚ አቶ ኤፍሬም ተስፋዬ ይህ እድል በመኖሩ በገበያው ውስጥ ያለው የትይዩ ገበያ ከጥቂት ጊዜ በኋላ እየከሰመ እንደሚሄድ ነግረውናል።


የዮጋ ፎሬክስ ቢሮ ስራ አስኪያጅ አቶ ፋሲል ሰለሞን በበኩላቸው በየቀኑ ለተጓዦች የተፈቀደውን የውጭ ምንዛሪ መጠን እንሸጣለን እንገዛለንም ሲሉ አስረድተውናል።


የውጭ ምንዛሪ እጥረት አለባችሁ ወይ ብለን ቢሮዎቹን መጠየቃችን አልቀረም።


ቢሮዎቹም ምንም አይነት የውጭ ምንዛሪ እጥረት የለብንም ደንበኞችም የቀድሞውን የባንክ አሰራር አስታሰውሰው በዚህ አገልግሎት ደስተኞች ናቸው ብለዋል።


አቶ ኤፍሬም ጨምረውም የጥቁር ገበያው እየከሰመ መሄዱ አይቀርም ይህ የበረንዳ ገበያም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚ አይናገርም፣ አያስረዳም ብለዋል።


ተህቦ ንጉሴ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page