top of page

የካቲት 13 2017 -በአዲስ አበባ በየቀኑ በአማካይ 7,183 አሽከርካሪዎች በትራፊክ ደንብ መተላለፍ በትራፊክ ፖሊስ ብቻ ይቀጣሉ።

በአዲስ አበባ በየቀኑ በአማካይ 7,183 አሽከርካሪዎች በትራፊክ ደንብ መተላለፍ በትራፊክ ፖሊስ ብቻ ይቀጣሉ።


ይህ በሌሎች የትራፊክ ደንብ ታላፊዎችን የሚቀጡትን አይጨምርም።


ባለፉት በስድስት ወራት ውስጥ በተለያዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች ከአንድ ሚሊየን ሁለት መቶ ዘጠና ሦስት ሺህ በላይ አሽከርካሪዎች በትራፊክ ፖሊስ አባላት ብቻ ተቀጥተዋል፡፡


ይህም በየቀኑ 7183 አሽካርካሪዎች መቀጣታቸውን ያሳያል፡፡


በሌላ በኩል የታጠፈ የደበዘዘ የተፋፋቀ እና በአጠቃላይ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ #ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ጥብቅ ቁጥጥር አደርጋለሁ ሲል የአዲስ አበባ ፖሊስ ተናግሯል፡፡


ባለፈው በጥር ወር ብቻ ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ በተደረገ ቁጥጥር ከ2,100 በላይ አሽከርካሪዎች ተቀጥተዋል ተብሏል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ በየጊዜው እየተባባሰ ለመጣው የመንገድ ትራፊክ አደጋ ልዩ ልዩ የደምብ መተላለፍ ጥፋቶች እንደ ምክንያትነት የሚገለጹ ቢሆንም ለእይታ ግልፅ ያልሆኑ የተሽከርካሪ ሰሌዳዎች መበራከት ለአደጋ ብቻ ሳይሆን የ #ወንጀል ስጋት እየሆኑ መምጣታቸውን ፖሊስ አስረድቷል፡፡


በየጊዜው የታጠፈ የደበዘዘ እና የተፋፋቀ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ህጋዊ እርምጃ እየተወሰደ ቢሆንም በሚፈለገው ደረጃ ችግሩን መቅረፍ አልተቻለም ያለው ፖሊስ አሁንም ጠንካራ የቁጥጥርና አደርጋለሁ ብሏል፡፡


ለዕይታ ግልፅ ያልሆነ ሰሌዳ ለጥፈው በሚንቀሳቀሱ አሽከርካሪዎች ላይ ጥፋቱ ለመጀመሪያ ጊዜ ከሆነ 1500 ብር ያስቀጣል፡፡


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page