የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሲስተም መቋረጥ እንዳጋጠመው ተናገረ፡፡
ይህ የሆነውም በባንኩ መረጃ ማስተላለፊያ የፋይበር ኦፕቲክስ ገመድ ላይ በደረሰ ጉዳት መሆኑን ባንኩ አስረድቷል፡፡
በዚህም ምክንያት በባንኩ በቅርንጫፎች፣ በኢንተርኔት ባንኪንግ፣ በሞባይል ባንኪንግ እንዲሁም ሲቢኢ ብር አገልግሎት ተቋርጧል ብሏል፡፡
አገልግሎቱን መልሶ ለማስጀመር ከሚመለከታቸው የባለድርሻ አካላት ጋር በጥምረት በከፍተኛ እርብርብ እየተሰራ ነው ያለው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፤ ደንበኞቹም በትዕግስት እንዲጠብቁ፣ ለተፈጠረው መጉላላትም ይቅርታ ጠይቋል፡፡

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
Telegram: https://tinyurl.com/yc6tfzsw
Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
Comments