top of page

የካቲት 12፣2016 - ቪዛ ካርድ(VISA) የኢትዮጵያን የዲጂታይዜሽን እቅድ እንዲሳካ የማደርገውን ድጋፍ እቀጥላለሁ አለ

በአለም ላይ የካርድ ባንኪንግ ከሚሰጡ ቀዳሚ ፊንቴኮች መካከል አንዱ የሆነው ቪዛ ካርድ(VISA) የኢትዮጵያን የዲጂታይዜሽን እቅድ እንዲሳካ የማደርገውን ድጋፍ እቀጥላለሁ አለ፡፡


ከተመሰረተ 60 ዓመት የሞላው እና ከሶስት ዓመት በፊት ጀምሮ በኢትዮጵያ መስራት የጀመረው ቪዛ፤ ኢትዮጵያን ማገዜን እገፋበታለሁ ያለው ባለፈው ሳምንት መጀመሪያ ላይ ዋና ስራ አስፈፃሚው ሪያን ማኪነርኒ ኢትዮጵያን በጎበኙበት ወቅት መሆኑን ሰምተናል፡፡


ዋና ስራ አስፈፃሚው ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ጋርም ተገናኝተው መወያየታቸው ይታወሳል፡፡

በውይይቱ ወቅትም ቪዛ የኢትጵያን የዲጅታል ኢኮኖሚ ግንባታ ለመደገፍ ቁርጠኛ መሆኑን ስራ አስፈጻሚው ለጠቅላይ ሚኒስተሩ አረጋግጠውላቸዋል ተብሏል፡፡


በዲጂታል ክፍያዎች እድገት፣ የፋይናንስ አካታችነትን በማጎልበት እና ለአነስተኛ እና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች፣ ለሴቶች እና ለወጣቶች ጠንካራ ድጋፍ ማድረግ በሚሉት ጉዳይች ላይ ውይይት ማድረጉን ቪዛ ለሸገር በላከው መግለጫ ጠቅሷል፡፡



"ቪዛ በኢትዮጵያ እና በመላው አፍሪካ ክፍያዎችን ዲጂታል ለማድረግ ቁርጠኛ ነው" ሲሉ ሪያን ማኪነርኒ አስረድተዋል።


በአፍሪካ ውስጥ ከሉት 10 መሥሪያ ቤቶች አንደኛውን በኢትዮጵያ ውስጥ ያደረገው ቪዛ የፋይናንስ ሥነ- ምህዳርን ለመደገፍ እና ለማጠናከር በርካታ ፕሮግራሞችን መጀመሩን ተናግሯል።


የዲጂታል ክፍያዎችን በማበርታት በኩል ከፋይናንስ ተቋማት እና ፊንቴኮች፣ ከብሔራዊ መታወቂያ ቦርድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ የአቢሲኒያ ባንክ እና የኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ ጋር እየሰራ መሆኑንም ኩባያው ጠቅሷል፡፡


ይህም ለተጠቃሚዎች በእጅ ስልኮቻቸው ደህንነቱ የተጠበቀ እና ምቹ የክፍያ ስዓት እንዲኖር አስችሏል ተብሏል፡፡


የግብይት ሥርዓቱን የሚያቀላጥፉ ፊንቴኮችን አወዳድሮ የሚሸልመው ቪዛ ኤቭሪዌር ኢኒሼቲቭ (Visa Everywhere Initiative) ሴቶችን ለመደገፍ የነደፈው ሺ ኢዝ ኔክስት(She is Next) ከሚሰራቸው ስራዎች መካከል ናቸው።


የቪዛ ካርድን የያዙ ከ 7 ሚሊዮን በላይ ደንበኞች በኢትዮጵያ አንዳሉት ደርጅቱ ተናግሯል፡፡




የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page