የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የስራ ዘመን ለአንድ ዓመት ተራዘመ።
የሕዝብ እነደራሴዎች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 4ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ አስቸኳይ ስብሰባው የኮሚሽኑ የስራ ዘመን እንዲራዘም የቀረበለትን የውሳኔ ሃሳብ አጽድቋል፡፡
ምክር ቤቱ ውሳኔውን ያሳለፈው የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን የሶስት ዓመታት የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ከቀረበለት በኋላ ነው፡፡

ኮሚሽኑ የቀሩትን ስራዎች ማጠናቀቅ ይችል ዘንድም የስራ ዘመኑ ለአንድ ዓመት እንዲራዘም ምክር ቤቱ በአብላጫ ድምፅ እና በሶስት ተቃውሞ አፅድቋል።
የምክር ቤቱ አባላት ኮሚሽኑ በተሰጠው ተጨማሪ የስራ ዘመን ቀሪ ስራዎችን እንዲያጠናቅቅ አሳስበዋል።
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments