የካቲት 10 2017 - ያለደረሰኝ ሲገበያዩ የተገኙ ከ2,900 በላይ ግለሰቦችና ተቋማት በገንዘብ ተቀጡ፡፡
- sheger1021fm
- Feb 17
- 1 min read
የአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ያለደረሰኝ የሚደረግ ግብይትን መልክ ለማስያዝ በሚል በጀመረው የቁጥጥር ስራ ያለደረሰኝ ሲገበያይ ያገኘሁትን 100 ሺህ ብር እቀጣለሁ ባልኩት መሰረት ቅጣቱን ተግባራዊ እያደረግኩ ነው ብሏል፡፡
በዚህ መሰረት በመንፈቅ ጊዜ ውስጥ 3,000 በላይ የንግድ ድርጅቶችና ግለሰቦችን አብዛኞቹን ማለትም 2,970ዎቹን እያንዳንዳቸውን 100,000 ብር በመቅጣት ከ297 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡንና የተቀሩትን 887ቱን ደግሞ በቃል ማስጠንቀቂያ ማለፉን ነግሮናል፡፡
ከአስተዳደራዊ እርምጃው ባሻገር ሌሎች 839 ግለሰቦች ደግሞ ጉዳያቸው በህግ እየታየ መሆኑን የገቢ አሰባሳቢ ቢሮው የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ነግረውናል፡፡
በ3 ወራት ጊዜ ውስጥ ሳይከፈል ለረጅም ጊዜ ተከማችቶ ከነበረ 11 ቢሊዮን ብር የግብር እዳ ከ6 ቢሊዮን ብር በላዩን ከፋናንስ ኢንቴሌጀንት አስተዳደር ጋር በመሆን አስከፍለናል ብለዋል፡፡
በመንፈቅ ጊዜ ውስጥ 111 ቢሊዮን ብር ከገቢ ግብር መሰብሰቡን የሚናገረው ቢሮው በጥር ወር ብቻ ከ12 ቢሊዮን ብር በላይ ሰብስቢያለሁ ብሏል፡፡
ምንታምር ፀጋው
Comments