አዋሽ ባንክ ከደንበኞቼ ጋር ያለኝን ግንኙነት ለማበርታት ያግዘኛል ያለውን የደንበኞች ሳምንት ማካሄድ ጀመረ፡፡
ይህንንም “ለላቀ የደንበኞች እርካታ እንተጋለን” የሚል መሪቃል ሰጥቶታል፡፡
የደንበኞች ሳምንት የማስጀመሪያ ስነ ሥርዓት በባንኩ ዋናው መስሪያ ቤት እና በሁሉም ቅርንጫፎች በዛሬው እለት ተጀምሯል፡፡
ፕሮግራሙ ለአንድ ሳምንት አንደሚቆይ ተነግሯል፡፡
ደንበኞች ከባንኩ ጋር ስለነበራቸው አብሮነት ማመስገን፣ ማክበር፣ ሁሉም የባንኩ የዋና መ/ቤት የሥራ ኃላፊዎች በባንኩ ቅርንጫፎች በአካል ተገኝተው በአገልግሎት አሰጣጥ ላይ ያሉ ክፍተቶችን በመለየትና ደንበኞችን ለሚያጋጥሟቸው ችግሮች መፍትሔ መስጠት፣በተለያየ ምክንያት ከባንኩ ጋር መስራት ያቆሙ ደንበኞች ጋር የነበረውን ግንኙነት ዳግም ማደስ የመርሃ ግብሩ ዋና ዋና ዓላማዎች መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

የአዋሽ ባንክ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ፀሀይ ሽፈራው "ባንኩ ከምስረታው ጊዜ ጀምሮ የደንበኞቹን ፍላጐት ለማርካት ደንበኞችን ማዕከል ያደረጉ ደንበኛ ተኮር አገልግሎቶችን እያቀረበ ሰላሳ ዓመታትን በስኬት ተጉዟል" ብለዋል።
ባንኩ ከ983 በላይ ቅርንጫፎች አንደሉት የተነገረ ሲሆን ደንበኞች የሳምንቱን ሰባቱንም ቀናት የ24 ሰዓት የተሟላ የባንክ አገልግሎት የሚያገኙበት ዲጂታል ቅርንጫፎችን በተለያዩ ትላልቅ የሀገሪቱ ከተሞች ከፍቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ እንደሚገኝ ዋና ራ አስፈጻሚው አስረድተዋል፡፡
በተጨማሪም ባንኩ ኤቲኤሞች፣ ፖስ ማሽኖች፣ አዋሽ ብር ፕሮ የሞባይል መተግበሪያ፣ የኤጀንሲ(ወኪል) ባንኪንግ እና ኢንተርኔት ባንኪንግ በመታገዝ ቀልጣፋ እና ሁሉን ያማከለ አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

ባንኩ በአሁኑ ወቅት ከ14 ሚሊዮን በላይ ደንበኞችን አሉኝ ያለ ሲሆን ከ 273 ቢሊዮን ብር በላይ የተቀማጭ ሂሣብ ማሰባሰብ መቻሉም ተጠቅሷል፡፡
የባንኩ ጠቅላላ ሀብት ድግሞ ከ397 ቢሊዮን ብር በላይ ደርሷል ተብሏል፡፡
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5r
Comments