top of page

የካቲት 10 2017 - በልዩ ልዩ ስብሰባዎችና ዝግጅቶች ካለፈው ጥር ወር አጋማሽ አንስቶ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ሲካሄዱ የቆየው ጉባኤ በትናንትናው እለት ተጠናቋል

  • sheger1021fm
  • Feb 17
  • 1 min read

በልዩ ልዩ ስብሰባዎችና ዝግጅቶች ካለፈው ጥር ወር አጋማሽ አንስቶ በአፍሪካ ህብረት አዳራሽ ሲካሄዱ የቆየው ጉባኤ በትናንትናው እለት ተጠናቋል፡፡


በቋሚ የአምባሳደሮች፣ ሚኒስትሮች እና የሀገር ተወካዮች እንደየደረጃው ሲካሄድ የሰነበተው የህብረቱ 38ኛው የህብረቱ ጉባኤ የተጠናቀቀው የጅቡቲውን የውጪ ጉዳይ እና አለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር መሀመድ አሊ የሱፍን ለህብረቱ ኮሚሽነርነት በመምረጥ ነበር፡፡


የዘንድሮው የህብረቱ 38ኛው የመሪዎች ጉባኤ ዋነኛ ትኩረት በቅኝ ግዛት ዘመን በአፍሪካዊያንና በትውልደ አፍሪካውያን ላይ ለደረሰው በደል ካሣን የሚጠይቅ መሪ ቃልን በመያዝ ነበር፡፡

በመሪዎቹ ጉባኤ ላይ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስቴር ዐቢይ አህመድም በመሪዎቹ የተወሰነው የካሣ ጥያቄ መሪ ቃሉን በሚመለከት ተናግረዋል፡፡


ለአስራ አምስት ደቂቃ በዘለቀው ጠንክራ ንግግራቸው ደግመው ደጋግመው ለመላው አለም የነፃነት ትግል ፈር ቀዳጅ ስለሆነው የአድዋ ድል የተናገሩት የባርባዶስ ጠቅላይ ሚኒስቴር ሚያ ሞቴሊ ናቸው፡፡


ጠቅላይ ሚኒስትሯ በአፍሪካ መሪዎች የተቀረፀው የካሣ ጥያቄ ጉዳይ የገንዘብ ጉዳይ ብቻ ሳይሆን ይቅርታ ከመጠየቅ ጀምራልም ሲሉ በንግግራቸው አክለዋል፡፡


ጉቴሬዝ በስልጣን ዘመናቸው የአፍሪካ መሪዎች ጥያቄ የሆነውን እና በመንግስታቱ ድርጅት የፀጥታው ም/ቤት ቋሚ መቀመጫ ለማግኘት የሚያደርጉትን ትግል ቢያንስ 2 መቀመጫዎችን እንዲያገኙ አብረው ትግል እንደሚያደርጉ ተናግሯል፡፡


የህብረቱን የመሪዎች ጉባኤ የተለያየ መልክ በተመለከተ የኔነህ ሲሳይ ተከታዩን አሰናድቷል፡፡


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ…



Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2025 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page