የካቲት 1 2017 - ''የተረሳንና ባለቤት ያጣን ሆነናል'' የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች
- sheger1021fm
- Feb 8
- 1 min read
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር እና ኦሮሚያ ክልል ከጥቂት ዓመታት በፊት የአስተዳደር ወሰን ማካለላቸው ይታወሳል፡፡
በዚሁ ጊዜ ወደ ኦሮሚያ የተካለሉ የኮዬ ፈቼ የጋራ መኖሪያ ቤት ነዋሪዎች ‘’የተረሳንና ባለቤት ያጣን ሆነናል’’ እያሉ ነው፡፡
የውሃ፣ የመብራት እና የመንገድ መሰረተ ልማት ሳይሟሉላቸው ወሰኑ መካለሉን ነዋሪዎ ነግረውናል፡፡
ታዲያ አሁን አካባቢውን የሚያስተዳድረውን አካል ሲጠይቁ ቤቱን የገነባው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ነው መሰረት ልማቱን ማሟላት ያለበት እየተባል ያለመፍትሄ አመታት እያለፉ ነው ይላሉ፡፡
ችግሩ የፉክክር ቤት ሳይዘጋ ያድራል ሆኖብናል ሲሉም ቅሬታቸውን ለሸገር ራዲዬ ነግረዋል፡፡
ንጋቱ ሙሉ
የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…
📌 YouTube: https://tinyurl.com/ky57kspd
📌 WhatsApp: https://tinyurl.com/ycxjmm3s
📌 Tiktok: https://bit.ly/44Dd6Il
📌 Linkedin : https://tinyurl.com/yhycs5rs
Commentaires