top of page

የኤ ኤፍ ጂ ኤርክራፍት ፋይናንስ ጀርመን (AFG) እህት ኩባንያ የሆነው ኤ ኤፍ ጂ አቪየሺን አየርላንድ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ሀገራት መግባቱን ተናገረ።

  • 5 days ago
  • 2 min read

የካቲት 24/2018


በአውሮፕላን ንግድና ሀብት አስተዳደር የሚታወቀው ኤ ኤፍ ጂ ኤርክራፍት ፋይናንስ ጀርመን (AFG) እህት ኩባንያ የሆነው ኤ ኤፍ ጂ አቪየሺን አየርላንድ ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በመላው አፍሪካ ሀገራት መግባቱን ተናገረ።


ኩባንያው  ለአፍሪካ ስራው ሲልም ሁለት ከፍተኛ ባለሞያዎቹን  በአፍሪካ ተገኝተው እንዲሰሩ እንደመደባቸው ባወጣው መግለጫ ተናግሯል።



AFG አቪዬሽን  አየርላንድ  የናይጄሪያው ካሊ ኤር ሁለት CRJ1000 አውሮፕላኖች ባለቤት እንዲሆን ማስቻሉን ተናግሯል።


በዚህም የተነሳ የአፍሪካ ሀገራት አየር መንገዶች፣ አፕሬተሮች፣ የመንግሥት እና የአቪዬሽን ዘርፍ ሀላፊዎች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለቸው ተረድቻለሁ ብሏል።


ይህ ፍላጎት የአፍሪካ የአቪዬሽን ዘርፍ በአለም አቀፍ ደረጃ  በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረ መምጣቱን ያሳል ሲልም ኩባንያው ባወጣው መግለጫ አስረድቷል።


የአፍሪካ የአቪዬሽን ዘርፍ ፍላጎትን ለሟሟላትም AFG አቪዬሽን አየርላንድ ሁለት ከፍተኛ ባለሞያዎቹን ወደ አፍሪካ በመላክ ከዘርፉ ተዋኒያን ጋር እንዲገናኙና እንዲሰሩ እንዳደረገ ተናግሯል።



በዚህም የኩባንያው የቢዝነስ አቪዬሽን ዋና ዳይሬክተር ክርስቲያን ሃትጄ እና ምክትል ዋና ስራ አስፈፃሚና ዋና ኦፕሬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት ሺኤኩማ ጌማዴ ተመድበዋል ተብሏል።


ሁለቱ ከፍተኛ ባለሞያዎች በአውሮፕላን ንግድ፣ሊዝ፣ፋይናንስ፣በአየር መንገድ የንግድ ስትራቴጂ እና የበረራ መዳረሻዎች ማስፉት ላይ ከፍተኛ ልምድ ያካበቱ እንደሆኑ ኩባንያው በመግለጫው ጠቅሷል።


ሁለቱ ባለሞያዎች በመጪዎቹ ወራት በአፍሪካ ሀገራት ጉዞ በማድረግ በአቪዬሽን ዘርፍ ከተሰማሩ ኩባንያዎች ጋር በቀጥታ ውይይት ለማድረግ ማሰባቸውም ተጠቅሷል።


የንግድ አውሮፕላኖች ግዢና ምደባ፣የግል ጄት ግብይትና የመዋቅር ስራ፣የፋይናንስ ሊዝ መፍትሔዎች ፣የበረራ ማዘመን ስትራቴጂ ፣የማማከር አገልግሎት ኩባንያው ከሚሰራዎች  ስራዎች መካከል መሆናቸው ተነግሯል።


"በአለም ላይ ከፍተኛ የአቪዬሽን እድገት እየታየባቸው ካሉት ውስጥ አፍሪካ ምሳሌ  ናት "ያሉት በኩባንያውን የአፍሪካ ስራ ለመምራት የተመደቡት ክርስቲያን ሃትጄ "እያየነው ያለውነው የተሳትፎ መጠን በአፍሪካ በአካል ተገኝተን ሁኔታዎችን ለማጤንና ዘላቂነት ያለው ትብብር ለመመስረት ያግዘናል" ብለዋል።


"በአፍሪካ ያየነው የትብብር ፍላጎት በጣም ከፍተኛ ነው። በአህጉሪቱ ዘላቂ የአቪዬሽን ልማት ለመደገፍ፣ የምክር አገልግሎት ለመስጠት፣ በግል አቪዬሽን እና ተያያዥ  ዘርፎች የኩባንያውን  የካበተ ልምድ ይዘን ወደ አፍሪካ ተቀላቅለናል'' ሲሉ ሺኤኩማ ጌማዴ ተናግረዋል።


በአፍሪካ አቪዬሽን ገበያ መግባቱን  የተናገረው AFG አቪዬሽን አየርላንድ "ኤርክራፍት ፋይናንስ ጀርመን (AFG) ኩባንያ እህት ኩባንያ ነው።


AFG በአለም ላይ በአውሮፕላን ንግድ እና ሀብት አስተዳደር  የሚታወቅ ኩባንያ ነው።


ንጋቱ ሙሉ

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page