top of page

የኤስኦኤስ የህፃናት መንደር (SOS Children's Villages)

  • sheger1021fm
  • Nov 25, 2025
  • 1 min read

ህዳር 16 2018

 

ለተለያየ ችግር የተጋለጡ ህፃናትን በምፈልገው ልክ እንዳላግዝ በሀገሪቱ ያሉ ግጭቶች እንቅፋት ሆነውብኛል ሲል በህፃናት ጥበቃ እና ልማት ዙሪያ የሚሰራው ኤስኦኤስ የህፃናት መንደር የተሰኘ ጅርጅት ተናገረ።

 

ግብረሰናይ ድርጅቱ ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች ስራዎቼን አንዴ እየጀመርኩ አንዴ እያቋረጥኩ ለመስራት ተገድጃለሁም ብሏል።

 

ይህንን የነገሩን የኤስኦኤስ የህፃናት መንደር (SOS Children's Villages) የኢትዮጵያ እና የደቡብ ሱዳን ብሔራዊ ዳይሬክተር ሳህለማርያም አበበ ናቸው።

 

ከአፋር፣ ከቤኒሻንጉልጉመዝ እና ከጋምቤል ክልሎች ውጪ በሁሉም የሀገሪቱ ክፍሎች ለችግር የተጋለጡ ህፃናት ላይ እየሰራን ነው ሲሉ አቶ ሳሀለማርያም ተናግዋል፡፡

በተለይ ግጭት በተደጋጋሚ በሚጎበኛቸው ትግራይ፣ አማራ እና ኦሮሚያ ክልሎች ያሉ ህፃናት የበለጠ ለችግር ሲጋለጡ በስራችን ወቅት ተመልክተናልም ብለውናል።

 

ድርጅቱ በኢትዮጵያ ላላፉት 51 ዓመታት በተለያየ ችግሮች ውስጥ ያሉ ህፃናትን ሲረዳ መቆየቱን ተነግሯል።

 

በእነዚህ 51 ዓመታትም 8 ሚሊዮን ሰዎችን ደግፌአለሁ ሲል ተናግሯል።

 

ከዚህ በፊት ለችግር የተጋለጡ ህፃነትና ቤተሰቦቻቸውን ለመርዳት ከውጭ ይመጣ የነበረው ርዳታ ጦርነት ወደተከሰተባቸው የአለም ሀገራት ስለተሸጋሸገ የፊይናንስ ችግርም እያጋጠማቸው እንደሆነ ዳይሬክተሩ አስረድተዋል።

 

ድርጅቱ በሀገሪቱ የሚገኙ ለተለያየ ችግር የተዳረጉ ህፃናትን ለመደገፍ የሀገር ውስጥ ለጋሽ ጋር በብርቱ ለመስራት አቅጃለሁ ሲልም ሰምተነዋል፡፡

 

ለዚሁ ይረዳውም ዘንድ ድርጅቱ በዛሬው ዕለት አርቲስት አለማየሁ ታደሰን በብራንድ አምባሳደርነት ሾሟል።


ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….

ማንያዘዋል ጌታሁን ያዘጋጀውን በፋሲካ ሙሉወርቅ

 

የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

👇👇👇

 

 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page