የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በተመድ በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ እንዲያደርጉ ተመደቡ፡፡
- Jun 25
- 1 min read
ሰኔ 18/2018
የቀድሞዋ የኢትዮጵያ ፕሬዚደንት አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት በምእራብ አፍሪካና ሳህል ቢሮ ውስጥ ገለልተኛ ስትራቴጂያዊ ግምገማ እንዲያደርጉ በተመድ ተመደቡ፡፡
አንጋፋዋ ዲፕሎማት በዲሱ ሹመታቸው ተቋሙ ለአካባቢው ቀውሶች በሚሰጠው ፈጣን ያልሆነ ምላሽ ሳቢያ የሚነሱበትን ትችቶችና የአሰራር ክፍተቶች መመርመር ነው ተብሏል።

አምባሳደሯ ለአዲሱ ስራ ወደ ዳካር ሴኔጋል በመጪው ወር ይጓዛሉ ተብሏል፡፡
አምባሳደር ሳህለወርቅ በፈረንሳይ፣በጅቡቲ የኢትዮጵያ አምባሳደር፣በተባበሩት መንግሥታት የትምህርት፣ ሳይንስና ባህል ድርጅት (ዩኔስኮ/UNESCO) እና በምሥራቅ አፍሪካ የልማት በይነ-መንግሥታት ባለሥልጣን (ኢጋድ/IGAD) ቋሚ መልዕክተኛ ሆነው ሰርተዋል፡፡
በ1942 በአዲስ አበባ ተወልደው ያደጉት የቀድሞዋ ረዕሰ ብሔር ሳህለወርቅ ዘውዴ ፈረንሳይ ከሚገኘው የሞንፔሊዬ ዩኒቨርሲቲ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የመጀመሪያ ዲግሪ ያላቸው ሲሆን የኢትዮጵያ የመጀመሪያዋ ሴት ፕሬዚዳንት በመሆን ከ 2011 እስከ ጥቅምት 2017 ያገለገሉ ዲፕሎማት ናቸው።
ንጋቱ ሙሉ





Comments