top of page

 የኢትዮዽያ የሎጅስቲክስ ስርዓት እና የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና

  • Dec 26, 2025
  • 1 min read

ታህሳስ 17/2018 

 

የአፍሪካ ነፃ የንግድ ቀጠና የሀገራትን የምርት ልውውጥ ለማሳደግ ኢኮኖሚያቸውን ይደግፋል ተብሎ ታምኖበታል፡፡

 

 ኢትዮዽያም በዚሁ መስመር ወደ ቀጠናው የንግድ እና ጭነት ስራ ጀምራለች።

 

ሆኖም የሎጀቲክስ ስራውም ጎን ለጎን ሊሰራበት እንደሚገባ ይመከራል።

 

ኢትዮጵያ ከ 90 በመቶ በላይ ጭነቶችን በመኪና ታጓጉዛለች፡፡

 

በቀጠናው ሀገራት ጋር የሚኖራትን የንግድ ግንኙነት በባቡር እና በሌሎች መንገዶች ብታቀላጥፍ ደግሞ ሎጀስቲክሱ ይበልጥ ውጤት ያመጣል።

 

ገቢ ወጭ እቃዎችን ከአንድ ላኪ ሐገር ወደ ኢትዮዽያ በባሕር፣ በአየር፣ በመሬት ወይም በባቡር ማቀላጠፍ የሎጀስቲክስ ዋና ዋና ስራዎችን ያቀላል።

በተለይ በኢትዮጵያ ከገቢና ወጭ ጭነት ጋር በተገናኘ ፤ የመሀል ሐገር ኢኮኖሚው የተሻለ ውጤት እንዲቆጠርበት ፤የጭነት መኪኖች የመጓጓዣ እና አጭር መንገድ መምረጥ ፤ የጉምሩክ ሰነዶችን ማዘጋጀት እና ቢሮክራሲ መቀነስ አስፈላጊ እንደሆነ እኛ የጠየቅናቸው ባለሙያ አቶ ዳዊት ውብሸት ይናገራሉ።

 

ኢትዮጵያም የንግድ እቃዎችን ከላኪ እና ተቀባይ ሀገሮች በቀላሉ እንዲደርሱ ለማድረግ ፖሊሲዎቿንና መመሪያዎቿን መፈታተሽ እንዳለባት ይታመናል፡፡

 

ሙሉ ዘገባውን ያድምጡ….. 


ተህቦ ንጉሴ


የሸገርን ወሬዎች፣ መረጃ እና ፕሮግራሞች ይከታተሉ…

  

  

Recent Posts

See All
በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም  ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ነሐሴ 7 2018 በአዲስ አበባ ቀላል ባቡር ሃዲዶች ላይ ለአካል ጉዳተኞች የተሰራው መወጣጫ(ራምፕ) ለዓመታት በመዘጋቱ አካል ጉዳተኞች ባቡር መጠቀም ለማቆም ተገደናል ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል። የሃዲዱ ጠባቂ የፀጥታ አካላት የተዘጋውን መወጣጫ(ራምፕ) እንዲከፍቱላቸው ቢጠይቁም የተሰጣቸው ምላሽ እስከ ድብደባ የደረሰ

 
 
 
የነሐሴ 7 2018 የውጪ ሀገር ወሬዎች

#ዩጋንዳ ዩጋንዳ ከአውሮፓ የሚባረሩ የ3ኛ አገር ስደተኞችን ልትቀበል ነው ተባለ፡፡ ዩጋንዳ ከአውሮፓ ተባራሪዎቹን ተቀብላ ለማስተናገድ መዘጋጀቷን ካቲሜሪኒ የተሰኘ የግሪክ ጋዜጣ መዘገቡን አናዶሉ ፅፏል፡፡ ጋዜጣው ዘገባውን ያሰራጨው ዲፕሎማሲያዊ ምንጮችን በዋቢነት በመጥቀስ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሐሳቡ ቀዳሚ አፍላቂዎች

 
 
 

Comments


Sheger App Logo
iOS Store
Google Play
  • Facebook
  • X
  • Youtube
  • TikTok
  • Telegram
  • Whatsapp

    ሸገር
102.1

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አዲስ የሬዲዮ አቀራረብ መላና አዲስ ቃና ይዞ የቀረበ በሀገሪቱ የሚዲያ ገበያ ላይ መሪ ሚና የሚጫወት ጣቢያ ነው፡፡

ሁሌም ከሸገር ጋር ሁኑ
ሸገር የእናንተ ነው
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር! 

Sheger Radio | Sheger 102.1FM  © 2026 Adey Tensae Media & Entertainment PLC.  

bottom of page